ሆሴዕ 12

1 ኤፍሬም የነፋስ እረኛ ነው፤

ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል፤

ሐሰትንና ዐመፅን ያበዛል።

ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋል፤

የወይራ ዘይትንም ወደ ግብፅ ይልካል።

2 እግዚአብሔርበይሁዳ ላይ የሚያቀርበው ክስ አለው፤

ያዕቆብንእንደ መንገዱ ይቀጣዋል፤

እንደ ሥራውም ይከፍለዋል።

3 በማሕፀን ሳለ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፤

ሙሉ ሰውም ሲሆን ከአምላክ ጋር ታገለ።

4 ከመልአኩም ጋር ታገለ፤ አሸነፈውም፤

በፊቱ ሞገስን ለማግኘት አልቅሶ ለመነው፣

እርሱንም በቤቴል አገኘው፤

በዚያም ከእርሱ ጋር ተነጋገረ፤

5 እርሱም ሁሉን የሚገዛ አምላክእግዚአብሔር፣

የሚታወቅበት ስሙምእግዚአብሔርነው።

6 ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤

ፍቅርንና ፍትሕን ጠብቅ፤

ዘወትርም በአምላክህ ታመን።

7 ነጋዴው በሐሰተኛ ሚዛን ይሸጣል፤

ማጭበርበርንም ይወዳል።

8 ኤፍሬም እንዲህ እያለ ይታበያል፤

“እኔ ባለጠጋ ነኝ፤ ሀብታምም ሆኛለሁ፤

ይህ ሁሉ ሀብት እያለኝ፣

ምንም ዐይነት በደል ወይም ኀጢአት አያገኙብኝም።”

9 “ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ፣አምላካችሁእግዚአብሔርእኔ ነኝ፤

በዓመት በዓላችሁ ቀን ታደርጉ እንደ ነበረው ሁሉ፣

እንደ ገና በድንኳኖች እንድትቀመጡ

አደርጋችኋለሁ።

10 ለነቢያት ተናገርሁ፤

ራእይንም አበዛሁላቸው፤

በእነርሱም በኩል በምሳሌ ተናገርሁ።

11 ገለዓድ ክፉ ነው፤

ሕዝቡም ከንቱ ናቸው፤

ኮርማዎችን በጌልገላ ይሠዋሉን?

መሠዊያዎቻቸው በታረሰ መሬት ላይ እንዳለ፣

የድንጋይ ክምር ይሆናሉ።

12 ያዕቆብ ወደ ሶርያሸሸ፤

እስራኤል ሚስት ለማግኘት ሲል አገለገለ፤

ዋጋዋንም ለመክፈል በጎችን ጠበቀ።

13 እግዚአብሔርበነቢይ አማካይነት እስራኤልን ከግብፅ አወጣ፤

በነቢይም በኩል ተንከባከበው።

14 ኤፍሬም ግን ክፉኛ አስቈጣው፤

ጌታውም የደም አፍሳሽነቱን በደል በላዩ ላይ ያደርግበታል፤

ስለ ንቀቱም የሚገባውን ይከፍለዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *