ሆሴዕ 3

የሆሴዕ ከሚስቱ ጋር መታረቅ

1 እግዚአብሔርእንዲህ አለኝ፤ “እርሷ በሌላ ሰው የምትወደድ አመንዝራ ብትሆንም፣ አሁንም ሂድና ሚስትህን ውደዳት፤ ወደ ሌሎች አማልክት ዘወር ቢሉና ለእነርሱም የተቀደሰውን የዘቢብ ጥፍጥፍ ቢወዱም፣እግዚአብሔርእስራኤላውያንን እንደ ወደዳቸው አንተም እርሷን ውደዳት።”

2 ስለዚህ በዐሥራ አምስት ሰቅል ጥሬ ብርና በአንድ ቆሮስ ተኩል መስፈሪያ ገብስ ገዛኋት።

3 እኔም፣ “ከእኔ ጋር ብዙ ቀን ተቀመጪ፤አታመንዝሪ ወይም ሌላ ሰው አትውደጂ፤ እኔም ከአንቺ ጋር እኖራለሁ” ብዬ ነገርኋት።

4 እስራኤላውያን ለብዙ ዘመን ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፣ ያለ መሥዋዕትና ያለ ዐምደ ጣዖት፣ ያለ ኤፉድና ያለ ጣዖት ምስል ይኖራሉና።

5 ከዚያ በኋላ እስራኤላውያን ተመልሰው አምላካቸውንእግዚአብሔርንናንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤ በመጨረሻውም ዘመን በመንቀጥቀጥ ወደእግዚአብሔርናወደ በረከቱ ይመጣሉ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *