በእስራኤል ላይ የቀረበ ክስ
1 በምድሪቱ በምትኖሩ በእናንተ ላይ
እግዚአብሔርየሚያቀርበው ክስ ስላለው፣
እናንት እስራኤላውያን ይህንየእግዚአብሔርንቃል ስሙ፤
“ታማኝነት የለም፤ ፍቅርም የለም፤
እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድሪቱ የለም።
2 በዚያ ያለው ርግማን፣መዋሸት፣ መግደል፣
መስረቅና ማመንዘር ብቻ ነው፤
ቃል ኪዳንን ሁሉ ያፈርሳሉ፤
ደም ማፍሰስና ግድያ ይበዛል።
3 ስለዚህ ምድሪቱ አለቀሰች፤
በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ኰሰመኑ፤
የምድር አራዊት፣ የሰማይ ወፎች፣
የባሕርም ዓሦች አለቁ።
4 “ነገር ግን ማንም ሰው አይከራከር፤
ማንም ሌላውን አይወንጅል፤
በካህናት ላይ ክስን እንደሚያቀርቡ፣
ሕዝብህ እንደዚያው ናቸውና።
5 ቀንና ሌሊት ትደናበራላችሁ፤
ነቢያትም ከእናንተ ጋር ይደናበራሉ፤
ስለዚህ እናታችሁን አጠፋታለሁ፤
6 ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል።
“ዕውቀትን ስለናቃችሁ፣
እኔም ካህናት እንዳትሆኑ ናቅኋችሁ፤
የአምላካችሁን ሕግ ስለ ረሳችሁ፣
እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።
7 ካህናት በበዙ ቊጥር፣
በእኔ ላይ የሚያደርጉት ኀጢአት በዝቶአል፤
ክብራቸውንምበውርደት ለውጠዋል።
8 የሕዝቤ ኀጢአት ለመብል ሆኖላቸዋል፤
ርኵሰታቸውንም እጅግ ወደዱ።
9 ካህናትም ከሕዝቡ የተለዩ አይደሉም፤
ሁሉንም እንደ መንገዳቸው እቀጣቸዋለሁ፤
እንደ ሥራቸውም እከፍላቸዋለሁ።
10 “ይበላሉ ግን አይጠግቡም፤
ያመነዝራሉ ግን አይበዙም፤
እግዚአብሔርንበመተው፣
ራሳቸውን
11 ለአመንዝራነት፣
ለአሮጌና ለአዲስ የወይን ጠጅ አሳልፈው ሰጡ፤
በእነዚህም
12 የሕዝቤ ማስተዋል ተወሰደ፤
ከዕንጨት የተሠራውን ጣዖት ምክር ይጠይቃሉ፤
ዘንጋቸውም ይመልስላቸዋል።
የአመንዝራነት መንፈስ ያስታቸዋል፤
ለአምላካቸውም ታማኝ አልሆኑም።
13 በተራሮችም ጫፍ ላይ ይሠዋሉ፤
መልካም ጥላ ባለው፣ በባሉጥ፣
በኮምቦልና በአሆማ ዛፍ ሥር፣
በኰረብቶችም ላይ የሚቃጠል ቊርባን ያቀርባሉ።
ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማዊ፣
ምራቶቻችሁም አመንዝራ ይሆናሉ።
14 “ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማውያን ሲሆኑ፣
የልጆቻችሁም ሚስቶች ሲያመነዝሩ
አልቀጣቸውም።
ወንዶች ከጋለሞቶች ጋር ይሴስናሉ፤
ከቤተ ጣዖት ዘማውያን ጋር ይሠዋሉና፤
የማያስተውል ሕዝብ ወደ ጥፋት ይሄዳል!
15 “እስራኤል ሆይ፤ አንቺ ብታመነዝሪም፣
ይሁዳ በበደለኛነት አትጠየቅ።
“ወደ ጌልገላ አትሂዱ፤
ወደ ቤትአዌንምአትውጡ፤
‘ሕያውእግዚአብሔርን’ ብላችሁም አትማሉ።
16 እስራኤላውያን እንደ እልኸኛ ጊደር፣
እልኸኞች ናቸው፤
ታዲያእግዚአብሔርእነርሱን በመልካም መስክ ውስጥ እንዳሉ የበግ ጠቦቶች
እንዴት ያሰማራቸዋል?
17 ኤፍሬም ከጣዖት ጋር ተጣምሮአል፤
እስቲ ተውት፤
18 መጠጣቸው ባለቀ ጊዜ እንኳ፣
ዘማዊነታቸውን አያቆሙም፤
ገዦቻቸውም ነውርን አጥብቀው ይወዳሉ።
19 ዐውሎ ነፋስ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል፤
መሥዋዕቶቻቸውም ኀፍረት ያመጡባቸዋል።