የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት የተደረገ ጥሪ
1 ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን፣ የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል ወደ ይሁዳ ገዥ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤልና ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱእንዲህ ሲል መጣ፤
2 እግዚአብሔርጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “ይህ ሕዝብ፣ ‘የእግዚአብሔርቤት የሚሠራበት ጊዜ ገና ነው’ ይላል።”
3 የእግዚአብሔርምቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል እንዲህ ሲል መጣ፤
4 “ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ፣ እናንተ ራሳችሁ በተዋቡ ቤቶቻችሁ ውስጥ ለመኖር ጊዜው ነውን?”
5 ስለዚህእግዚአብሔርጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “እስቲ መንገዳችሁን ልብ በሉ፤
6 ብዙ ዘራችሁ፤ ነገር ግን ያጨዳችሁት ጥቂት ነው፤ በላችሁ ግን አልጠገባችሁም፤ ጠጣችሁ ግን አልረካችሁም፤ ለበሳችሁ ግን አልሞቃችሁም፤ ደመወዝን ተቀበላችሁ፤ ግን በቀዳዳ ኰረጆ የማስቀመጥ ያህል ነው።”
7 እግዚአብሔርጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “እስቲ መንገዳችሁን ልብ በሉ፤
8 ወደ ተራራ ውጡ፤ ዕንጨት አምጡ፤ ቤቱን ሥሩ፤ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፤ እከበርበታለሁም” ይላልእግዚአብሔር።
9 ሁሉን የሚገዛእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ “ብዙ ተስፋ አደረጋችሁ፤ ያገኛችሁት ግን ጥቂት ነው፤ ወደ ቤት ያስገባችሁትንም እኔ እፍ አልሁበት፤ ይህ የሆነው ለምን ይመስላችኋል?” የእኔ ቤት ፈርሶ እያለ ሁላችሁም የራሳችሁን ቤት ለመሥራት ስለሮጣችሁ ነው፤
10 ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ሰማያት ጠል ከለከሉ፤ ምድርም ፍሬዋን ነሣች።
11 እኔም በዕርሻዎችና በተራሮች፣ በእህሉና በአዲሱ ወይን ጠጅ፣ በዘይቱና ምድር በምታፈራው ሁሉ፣ በሰውና በእንስሳ፣ በእጆቻችሁም ሥራ ላይ ድርቅ አመጣሁ።”
12 ከዚህ በኋላ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል፣ ሊቀ ካህናቱ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፣ ከምርኮ የተረፉትም ሕዝብ የአምላካቸውንየእግዚአብሔርንድምፅ፣ የነቢዩንም የሐጌን መልእክት ሰሙ፤ አምላካቸውእግዚአብሔርልኮታልና። ሕዝቡምእግዚአብሔርንፈሩ።
13 ቀጥሎምየእግዚአብሔርመልእክተኛ ሐጌ፣ ይህንየእግዚአብሔርንመልእክት ለሕዝቡ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ” ይላልእግዚአብሔር።
14 ስለዚህእግዚአብሔርየይሁዳን ገዥ፣ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፣ የሊቀ ካህናቱን የኢዮሴዴቅን ልጅ፣ የኢያሱን መንፈስና፣ ከምርኮ የተረፈውን ሕዝብ ሁሉ መንፈስ አነሣሣ፤ እነርሱም መጥተው የአምላካቸውንየእግዚአብሔርጸባኦት ቤት መሥራት ጀመሩ።
15 ይህ የሆነውም ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ በሃያ አራተኛው ቀን ነበር።