ስለ ግብፅ የወጣ ሙሾ
1 የእግዚአብሔርቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
2 “የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤
“ ‘ዋይ! በል፤ እንዲህም በል፤
“ወዮ ለዚያ ቀን!”
3 ቀኑ ቅርብ ነው፤
የእግዚአብሔርቀን ቅርብ ነው፤
የደመና ቀን፣
ለአሕዛብም የጥፋት ቀን ነው።
4 በግብፅ ላይ ሰይፍ ይሆናል፤
በኢትዮጵያም ላይ ጭንቀት ይመጣል።
የታረዱት በግብፅ ሲወድቁ፣
ሀብቷ ይወሰዳል፤
መሠረቶቿም ይፈርሳሉ።
5 ኢትዮጵያና ፉጥ፣ ልድያና መላው ዐረብ፣ ሊብያናየቃል ኪዳኑ ምድር ሕዝብ ከግብፅ ጋር በአንድነት በሰይፍ ይወድቃሉ።
6 “ ‘እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤
“ ‘የግብፅ ተባባሪዎች ይወድቃሉ።
የምትኵራራበት ብርታቷ ይወድቃል።
ከሚግዶል እስከ አስዋን፣
በውስጧ በሰይፍ ይወድቃሉ፤
ይላል ጌታእግዚአብሔር።
7 “ ‘በባድማ መሬቶች መካከል፣
ባድማ ይሆናሉ፤
ከተሞቻቸውም፣
ከፈራረሱ ከተሞች መካከል ይሆናሉ።
8 በግብፅ ላይ እሳት ስጭር፣
ረዳቶቿ ሁሉ ሲደቁ፣
በዚያን ጊዜ እኔእግዚአብሔርእንደሆንሁ ያውቃሉ፤
9 “ ‘በዚያ ቀን ከእኔ ዘንድ መልእክተኞች በመርከብ ወጥተው ተዘልላ ከተቀመጠችበት ሁኔታ ለማውጣት ኢትዮጵያን ያስፈራሯታል፤ ግብፅ በጨለማ በምትዋጥበት ቀን ጭንቅ ይይዛቸዋል፤ ቀኑ በእርግጥ ይመጣልና።
10 “ ‘ጌታእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤
“ ‘በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ፣
ስፍር ቍጥር የሌለውን የግብፅን ሕዝብ እደመስሳለሁ።
11 ከአሕዛብ ሁሉ እጅግ ጨካኝ የሆኑት፣ እርሱና ሰራዊቱ፣
ምድሪቱን ለማጥፋት እንዲመጡ ይደረጋል፤
ሰይፋቸውን በግብፅ ላይ ይመዛሉ፤
ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋሉ፤
12 የዐባይን ወንዝ ውሃ አደርቃለሁ፤
ምድሪቱን ለክፉ ሰዎች እሸጣለሁ፤
በባዕዳን እጅ፣ ምድሪቷንና በውስጧ
ያለውን ሁሉ ባድማ አደርጋለሁ፤
እኔእግዚአብሔርተናግሬአለሁ።
13 “ ‘ጌታእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤
“ ‘ጣዖታትን አጠፋለሁ፤
በሜምፊስያሉትን ምስሎች እደመስሳለሁ።
ከእንግዲህ በግብፅ ገዥ አይኖርም፣
በምድሪቱም ላይ ፍርሀት እሰዳለሁ።
14 ጳፕሮስን ባድማ አደርጋለሁ፤
በጣኔዎስ ላይ እሳት እለኵሳለሁ፤
በቴብስላይ ቅጣት አመጣለሁ።
15 የግብፅ ምሽግ በሆነችው፣
በሲን ላይ መዓቴን አፈሳለሁ፤
ስፍር ቍጥር የሌለውን የቴብስን ሕዝብ አጠፋለሁ።
16 በግብፅ ላይ እሳት አነዳለሁ፤
ሲን በጭንቅ ትናጣለች፤
ቴብስ በማዕበል ትወሰዳለች፤
ሜምፊስ በማያቋርጥ ጭንቀት ውስጥ ትገባለች።
17 የሄልዮቱናየቡባስቱጐልማሶች፣
በሰይፍ ይወድቃሉ፤
ከተሞቹ ራሳቸውም ይማረካሉ።
18 የግብፅን ቀንበር በምሰብርበት ጊዜ፣
በጣፍናስ ቀኑ ይጨልማል፤
ከዚያም የተኵራራችበት ብርታት ይንኰታኰታል።
በደመና ትሸፈናለች፤
መንደሮቿም ይማረካሉ።
19 ስለዚህ በግብፅ ላይ ቅጣቴን አመጣለሁ፤
እነርሱም እኔእግዚአብሔርእንደሆንሁ ያውቃሉ።’ ”
20 በዐሥራ አንደኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር በሰባተኛው ቀን፣የእግዚአብሔርቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
21 “የሰው ልጅ ሆይ፤ የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንን ክንድ ሰብሬአለሁ፤ ይፈወስ ዘንድ ክንዱ አልተጠገነም፤ ወይም ሰይፍ መያዝ ይችል ዘንድ እጁ በመቃ አልታሰረም።
22 ስለዚህ ጌታእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ተነሥቻለሁ፤ ደኅናውንና የተሰበረውን፣ ሁለቱንም ክንዶቹን እሰብራለሁ፤ ሰይፉም ከእጁ እንዲወድቅ አደርጋለሁ።
23 ግብፃውያንን በሕዝቦች መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ።
24 የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ ሰይፌንም አስይዘዋለሁ፤ የፈርዖንን ክንድ ግን እሰብራለሁ፤ እርሱም በፊቱ ክፉኛ እንደ ቈሰለ ሰው ያቃስታል።
25 የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ የፈርዖን ክንድ ግን ይዝላል፤ ሰይፌን በባቢሎን ንጉሥ እጅ ሳስይዝ፣ እርሱም ሲነቀንቀው፣ ያኔእግዚአብሔርመሆኔን ያውቃሉ።
26 በሕዝቦች መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ፤ ከዚያም እኔእግዚአብሔርመሆኔን ያውቃሉ።”