እግዚአብሔርን ለማመስገን የቀረበ ግብዣ
የምስጋና መዝሙር
1 ምድር ሁሉለእግዚአብሔርእልል በሉ፤
2 እግዚአብሔርንበደስታ አገልግሉት፤
በፍስሓ ዝማሬ ፊቱ ቅረቡ።
3 እግዚአብሔርአምላክ መሆኑን ዕወቁ፤
እርሱ ፈጠረን፤ እኛም የእርሱ ነን፤
እኛ ሕዝቡ የማሰማሪያው በጎች ነን።
4 በምስጋና ወደ ደጆቹ፣
በውዳሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፤
አመስግኑት፤ ስሙንም ባርኩ፤
5 እግዚአብሔርቸር፣ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና፤
ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።