መዝሙር 103

እግዚአብሔር ፍቅር ነው

የዳዊት መዝሙር

1 ነፍሴ ሆይ፤እግዚአብሔርንባርኪ

የውስጥ ሰውነቴም ሁሉ ቅዱስ ስሙን ባርኪ።

2 ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤

ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፤

3 ኀጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፣

ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፣

4 ሕይወትሽን ከጥፋት ጒድጓድ የሚያድን፣

ምሕረትንና ርኅራኄን የሚያቀዳጅሽ፣

5 ጐልማሳነትሽም እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ፣

ምኞትሽን በበጎ ነገር የሚያረካ እርሱ ነው።

6 እግዚአብሔርለተጨቈኑ ሁሉ፣

ቅን ፍርድንና ፍትሕን ይሰጣቸዋል።

7 መንገዱን ለሙሴ፣

ሥራውንም ለእስራኤል ሕዝብ አሳወቀ።

8 እግዚአብሔርመሓሪና ይቅር ባይ፣

ለቍጣ የዘገየ፣ ፍቅሩም የበዛ ነው።

9 እርሱ ሁል ጊዜ በደልን አይከታተልም፤

ለዘላለምም አይቈጣም።

10 እንደ ኀጢአታችን አልመለሰልንም፤

እንደ በደላችንም አልከፈለንም።

11 ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣

እንዲሁ ለሚፈሩት ምሕረቱ ታላቅ ናት።

12 ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፣

መተላለፋችንን በዚያው መጠን ከእኛ አስወገደ።

13 አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፣

እግዚአብሔርለሚፈሩት እንዲሁ ይራራል።

14 እርሱ አፈጣጠራችንን ያውቃልና፤

ትቢያ መሆናችንንም ያስባል።

15 ሰው እኮ ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤

እንደ ዱር አበባ ያቈጠቍጣል፤

16 ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ግን ድራሹ ይጠፋል፤

ምልክቱም በቦታው አይገኝም።

17 የእግዚአብሔርምሕረት ግን፣

ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ ነው፤

ጽድቁም እስከ ልጅ ልጅ ድረስ በላያቸው ይሆናል፤

18 ኪዳኑን በሚጠብቁት ላይ፣

ትእዛዙንም ለመፈጸም በሚተጉት ላይ ይሆናል።

19 እግዚአብሔርዙፋኑን በሰማይ አጽንቶአል፤

መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች።

20 እናንተ ለቃሉ የምትታዘዙ መላእክቱ፤

ትእዛዙንም የምትፈጽሙ እናንተ ኀያላን፤

እግዚአብሔርንባርኩ።

21 እናንተ ፈቃዱን የምትፈጽሙ አገልጋዮቹ፤

ሰራዊቱ ሁሉ፣እግዚአብሔርንባርኩ።

22 እናንተ በግዛቱ ሁሉ የምትኖሩ፣

ፍጥረቱ ሁሉ፣እግዚአብሔርንባርኩ፤

ነፍሴ ሆይ፤እግዚአብሔርንባርኪ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *