አንዱ እውነተኛው አምላክ
1 ለእኛ ሳይሆን፣እግዚአብሔርሆይ፤ ለእኛ ሳይሆን፣
ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህ፣
ለስምህ ክብርን ስጥ።
2 አሕዛብ፣ “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ?
3 አምላካችንስ በሰማይ ነው፤
እርሱ ደስ የሚለውን ያደርጋል።
4 የእነርሱ ጣዖታት ግን የሰው እጅ የሠራቸው፣
ብርና ወርቅ ናቸው።
5 አፍ አላቸው፤ አይናገሩም፤
ዐይን አላቸው፤ አያዩም፣
6 ጆሮ አላቸው፤ አይሰሙም፤
አፍንጫ አላቸው፤ አያሸቱም፤
7 እጅ አላቸው፤ አይዳስሱም፤
እግር አላቸው፤ አይሄዱም፤
በጒሮሮአቸውም ድምፅ አይፈጥሩም።
8 እነዚህን የሚያበጁ፣
የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።
9 የእስራኤል ቤት ሆይ፤በእግዚአብሔርታመኑ፤
ረዳታቸውና ጋሻቸው እርሱ ነው።
10 የአሮን ቤት ሆይ፤በእግዚአብሔርታመኑ፤
ረዳታቸውና ጋሻቸው እርሱ ነው።
11 እናንተእግዚአብሔርንየምትፈሩ ሆይ፤በእግዚአብሔርታመኑ፤
ረዳታቸውና ጋሻቸው እርሱ ነው።
12 እግዚአብሔርያስበናል፤ ይባርከናልም፤
እርሱ የእስራኤልን ቤት ይባርካል፤
የአሮንንም ቤት ይባርካል።
13 እግዚአብሔርንየሚፈሩትን ሁሉ፣
ትልቁንም ትንሹንም ይባርካል።
14 እግዚአብሔርእናንተንና ልጆቻችሁን፣
በባርኮቱ ያብዛችሁ።
15 ሰማይንና ምድርን በፈጠረ፣
በእግዚአብሔርየተባረካችሁ ሁኑ።
16 ሰማየ ሰማያትየእግዚአብሔርናቸው፤
ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።
17 እግዚአብሔርንየሚያመሰግኑት የሞቱት አይደሉም፤
ወደ ዝምታው ዓለም የሚወርዱም አይደሉም።
18 ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣
እግዚአብሔርንየምንባርክ እኛ ነን።
እግዚአብሔርይመስገን።