የሰላም ፀሮች
መዝሙረ መዓርግ
1 በተጨነቅሁ ጊዜ ወደእግዚአብሔርተጣራሁ፤
እርሱም መለሰልኝ።
2 እግዚአብሔርሆይ፤ ከሐሰተኛ ከንፈር፣
ከአታላይ ምላስም አድነኝ።
3 ሐሰተኛ አንደበት ሆይ፤ ምን ይከፈልህ?
ከዚህስ የባሰ ምን ይደረግብህ?
4 በተሳለ የጦረኛ ቀስት፣
በግራር ከሰል ፍም ይቀጣሃል።
5 በሜሼክ እኖራለሁና፣ በቄዳር ድንኳኖች መካከል እቀመጣለሁና ወዮልኝ!
6 ሰላምን በሚጠሉ መካከል፣
ነፍሴ እጅግ ብዙ ጊዜ ኖረች።
7 እኔ ሰላም ፈላጊ ነኝ፤
እነርሱ ግን በተናገርሁ ጊዜ ጠብ ይሻሉ።