ኢየሩሳሌም እልል በዪ!
የዳዊት መዝሙረ መዓርግ
1 “ወደእግዚአብሔርቤት እንሂድ” ባሉኝ ጊዜ፣
ደስ አለኝ።
2 ኢየሩሳሌም ሆይ፤ እግሮቻችን ከደጅሽ ውስጥ ቆመዋል።
3 ኢየሩሳሌም እጅግ እንደ ተጠጋጋች፣
ከተማ ሆና ተሠርታለች።
4 ለእስራኤል በተሰጠው ሥርዐት መሠረት፣
የእግዚአብሔርንስም ለማመስገን፣
የእግዚአብሔርነገዶች፣
ወደዚያ ይመጣሉ።
5 በዚያም የፍርድ ዙፋኖች የሆኑት፣
የዳዊት ቤት ዙፋኖች ተዘርግተዋል።
6 እንዲህ ብላችሁ ለኢየሩሳሌም ሰላም ጸልዩ፤
“የሚወዱሽ ይለምልሙ፤
7 በቅጥርሽ ውስጥ ሰላም ይሁን፤
በምሽግሽም ውስጥ መረጋጋት ይስፈን”።
8 ስለ ወንድሞቼና ስለ ባልንጀሮቼ፣
“በውስጥሽ ሰላም ይስፈን” እላለሁ።
9 ስለ አምላካችን ስለእግዚአብሔርቤት፣
በጎነትሽን እሻለሁ።