መዝሙር 124

የእስራኤል አዳኝ

የዳዊት መዝሙረ መዓርግ

1 እስራኤል እንዲህ ይበል፦

“እግዚአብሔርከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ፣

2 ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፣

እግዚአብሔርከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ፣

3 ቍጣቸው በላያችን በነደደ ጊዜ፣

በቁመናችን በዋጡን ነበር፤

4 ጐርፍ ባጥለቀለቀን፣

ፈረሰኛው ውሃ ባሰጠመን፣

5 ደራሽ ውሃም ጠራርጎ በወሰደን ነበር።

6 በጥርሳቸው ከመዘንጠል የጠበቀን፣

እግዚአብሔርይባረክ።

7 ነፍሳችን እንደ ወፍ፣

ከዐዳኝ ወጥመድ አመለጠች፤

ወጥመዱ ተሰበረ፤

እኛም አመለጥን።

8 የሰማይና የምድር ፈጣሪ፣

የእግዚአብሔርስም ረዳታችን ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *