እግዚአብሔር የሚታመኑበትን ይጠብቃል
መዝሙረ መዓርግ
1 በእግዚአብሔርየሚታመኑ፣
ሳትናወጥ ለዘላለም እንደምትኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው።
2 ተራሮች ኢየሩሳሌምን እንደ ከበቧት፣
ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣እግዚአብሔርበሕዝቡ ዙሪያ ነው።
3 ጻድቃን እጃቸውን፣ ለክፋት እንዳያነሡ፣
የክፉዎች በትረ መንግሥት፣
ለጻድቃን በተመደበች ምድር ላይ አያርፍም።
4 እግዚአብሔርሆይ፤ መልካም ለሆኑ፣
ልባቸውም ለቀና መልካም አድርግ።
5 ወደ ጠማማ መንገዳቸው የሚመለሱትን ግን፣
እግዚአብሔርከክፉ አድራጊዎች ጋር ያስወግዳቸዋል።
በእስራኤል ላይ ሰላም ይውረድ።