በእግዚአብሔር መታመን
የሰሎሞን መዝሙረ መዓርግ
1 እግዚአብሔርቤትን ካልሠራ፣
ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤
እግዚአብሔርከተማን ካልጠበቀ፣
ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።
2 የዕለት ጒርስ ለማግኘት በመጣር፣
ማልዳችሁ መነሣታችሁ፣
አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው፤
እርሱ ለሚወዳቸው እንቅልፍን ያድላልና።
3 እነሆ፤ ልጆችየእግዚአብሔርስጦታ ናቸው፤
የማሕፀንም ፍሬ ከቸርነቱ የሚገኝ ነው።
4 በወጣትነት የተገኙ ወንዶች ልጆች፣
በጦረኛ እጅ እንዳሉ ፍላጾች ናቸው።
5 ኰረጆዎቹ በእነዚህ የተሞሉ፣
የተባረከ ሰው ነው፤
ከጠላቶቻቸው ጋር በአደባባይ በሚሟ
ገቱበት ጊዜ፣ አይዋረዱም።