የጻድቃን በረከት
መዝሙረ መዓርግ
1 እግዚአብሔርንየሚፈሩ ሁሉ፣
በመንገዱም የሚሄዱ የተባረኩ ናቸው።
2 የድካምህን ፍሬ ትበላለህ፤
ትባረካለህ፤ ይሳካልሃልም።
3 ሚስትህ በቤትህ፣
እንደሚያፈራ ወይን ናት፤
ወንዶች ልጆችህ በማእድህ ዙሪያ፣
እንደ ወይራ ተክል ናቸው።
4 እነሆ፤እግዚአብሔርንየሚፈራ ሰው፣
እንዲህ ይባረካል።
5 እግዚአብሔርከጽዮን ይባርክህ፤
በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፣ የኢየሩሳሌምን ብልጽግና ያሳይህ፤
6 የልጅ ልጅ ለማየትም ያብቃህ።
በእስራኤል ላይ ሰላም ይውረድ።