የክብረ በዓል መዝሙር
መዝሙረ መዓርግ
1 እግዚአብሔርሆይ፤ ዳዊትን፣
የታገሠውንም መከራ ሁሉ ዐስብ፤
2 እርሱለእግዚአብሔርማለ፤
ለያዕቆብም ኀያል አምላክ እንዲህ ሲል ተሳለ፤
3 “ወደ ቤቴ አልገባም፤
ዐልጋዬም ላይ አልወጣም፤
4 ለዐይኖቼ እንቅልፍን፣
ለሽፋሽፍቶቼም ሸለብታ አልሰጥም፤
5 ለእግዚአብሔርስፍራን፣
ለያዕቆብም ኀያል አምላክ ማደሪያን እስካገኝ ድረስ።”
6 እነሆ፤ በኤፍራታ ሰማነው፤
በቂርያትይዓሪምአገኘነው።
7 “ወደ ማደሪያው እንግባ፤
እግሮቹ በሚቆሙበት ቦታ እንስገድ።
8 እግዚአብሔርሆይ፤ ተነሥ፤
አንተና የኀይልህ ታቦት ወደ ማረፊያህ ስፍራ ሂዱ።
9 ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፤
ቅዱሳንህም እልል ይበሉ።”
10 ስለ አገልጋይህ ስለ ዳዊት ስትል፣
የቀባኸውን ሰው አትተወው።
11 እግዚአብሔርለዳዊት በእውነት ማለ፤
በማይታጠፍም ቃሉ እንዲህ አለ፤
“ከገዛ ራስህ ፍሬ፣
በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።
12 ወንዶች ልጆችህ ኪዳኔን፣
የማስተምራቸውንም ምስክርነቴን ቢጠብቁ፣
ልጆቻቸው በዙፋንህ ላይ፣
ለዘላለም ይቀመጣሉ።
13 እግዚአብሔርጽዮንን መርጦአታልና፣
ማደሪያውም ትሆን ዘንድ ወዶአልና እንዲህ አለ፤
14 “ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤
ፈልጌአታለሁና በእርሷ እኖራለሁ።
15 እጅግ አትረፍርፌ እባርካታለሁ፤
ድኾቿን እንጀራ አጠግባለሁ።
16 ለካህናቷ ድነትን አለብሳለሁ፤
ቅዱሳኗም በደስታ ይዘምራሉ።
17 “በዚህም ለዳዊት ቀንድአበቅላለሁ፤
ለቀባሁትም ሰው መብራት አዘጋጃለሁ።
18 ጠላቶቹን ኀፍረት አከናንባቸዋለሁ፤
እርሱ ግን በራሱ ላይ የደፋው ዘውድ ያበራል።