የምስጋና መዝሙር
1 ሃሌ ሉያ።
የእግዚአብሔርንስም ወድሱ፤
እናንትየእግዚአብሔርአገልጋዮች ሆይ፤ አመስግኑት፤
2 በእግዚአብሔርቤት፣
በአምላካችን ቤት አደባባይ የምትቆሙ አመስግኑት።
3 እግዚአብሔርቸር ነውናእግዚአብሔርንአመስግኑ፤
መልካም ነውና፣ ለስሙ ዘምሩ፤
4 እግዚአብሔርያዕቆብን ለራሱ፣
እስራኤልንም ውድ ንብረቱ አድርጎ መርጦአልና።
5 እግዚአብሔርታላቅ እንደሆነ፣
ጌታችንም ከአማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ ዐውቃለሁና።
6 በሰማይና በምድር፣
በባሕርና በጥልቅ ሁሉ ውስጥ፣
እግዚአብሔርደስ ያሰኘውን ሁሉ ያደርጋል።
7 እርሱ ደመናትን ከምድር ዳርቻ ያስነሣል፤
መብረቅ ከዝናብ ጋር እንዲወርድ ያደርጋል፤
ነፋሳትንም ከማከማቻው ያወጣል።
8 በኵር ሆኖ በግብፅ የተወለደውን፣
ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ቀሠፈ።
9 ግብፅ ሆይ፤ በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ሁሉ ላይ፣
በመካከልሽ ታምራትንና ድንቅን ሰደደ።
10 ብዙ ሕዝቦችን መታ፤
ኀያላን ነገሥታትንም ገደለ።
11 የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፣
የባሳንን ንጉሥ ዐግን፣
የከነዓንን ነገሥታት ሁሉ ገደለ፤
12 ምድራቸውንም ርስት አድርጎ፣
ለሕዝቡ ርስት እንዲሆን ለእስራኤል ሰጠ።
13 እግዚአብሔርሆይ፤ ስምህ ዘላለማዊ ነው፤
እግዚአብሔርሆይ፤ መታሰቢያህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።
14 እግዚአብሔርለሕዝቡ ይፈርዳልና፣
ለአገልጋዮቹም ይራራላቸዋል።
15 የአሕዛብ ጣዖታት ከብርና ከወርቅ የተሠሩ፣
የሰው እጅ ያበጃቸው ናቸው።
16 አፍ አላቸው፤ አይናገሩም፤
ዐይን አላቸው፤ አያዩም፤
17 ጆሮ አላቸው፤ አይሰሙም፤
በአፋቸውም እስትንፋስ የለም።
18 እነዚህን የሚያበጁ፣
የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።
19 የእስራኤል ቤት ሆይ፤እግዚአብሔርንባርኩ፤
የአሮን ቤት ሆይ፤እግዚአብሔርንባርኩ፤
20 የሌዊ ቤት ሆይ፤እግዚአብሔርንባርኩ፤
እግዚአብሔርንየምትፈሩ ሆይ፤እግዚአብሔርንባርኩ።
21 በኢየሩሳሌም የሚኖርእግዚአብሔር፣ ከጽዮን ይባረክ።
ሃሌ ሉያ።