መዝሙር 137

የግዞተኞች ቅኔ

1 በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣ በዚያ ተቀምጠን ሳለን፣

ጽዮን ትዝ ባለችን ጊዜ አለቀስን።

2 እዚያም በአኻያ ዛፎች ላይ፣

በገናዎቻችንን ሰቀልን።

3 የማረኩን በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤

የሚያሠቃዩን የደስታ ዜማ ፈለጉብን፤

ደግሞም፣ “ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን” አሉን።

4 የእግዚአብሔርንዝማሬ፣

እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምር!

5 ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ብረሳሽ፣

ቀኝ እጄ ትክዳኝ።

6 ሳላስታውስሽ ብቀር፣

ኢየሩሳሌምን የደስታዬ ቍንጮ ባላደርግ፣

ምላሴ ከትናጋዬ ጋር ትጣበቅ።

7 እግዚአብሔርሆይ፤ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀን፣

ኤዶማውያን እንዴት እንደ ዛቱ ዐስብ፤

ደግሞም፣ “አፍርሷት፤

ፈጽማችሁ አፈራርሷት!” አሉ።

8 አንቺ አጥፊ የሆንሽ የባቢሎን ልጅ ሆይ፤

በእኛ ላይ ስለ ፈጸምሺው ድርጊት፣

የእጅሽን የሚሰጥሽ የተመሰገነ ነው፤

9 ሕፃናትሽንም ይዞ፣

በዐለት ላይ የሚፈጠፍጥ የተመሰገነ ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *