መዝሙር 138

የምስጋና መዝሙር

የዳዊት መዝሙር

1 እግዚአብሔር ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤

በአማልክት ፊት በመዝሙር እወድስሃለሁ።

2 ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤

ስለ ምሕረትህና ስለ ታማኝነትህ፣

ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፤

ስምህንና ቃልህን፣

ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ አድርገሃልና።

3 በጠራሁህ ቀን መልስ ሰጠኸኝ፤

ነፍሴን በማደፋፈርም ብርቱ አደረግኸኝ።

4 እግዚአብሔርሆይ፤ የአፍህን ቃል በሰሙ ጊዜ፣ የምድር ነገሥታት ሁሉ

ያመስግኑህ።

5 የእግዚአብሔርክብር ታላቅ ነውና፣

ስለእግዚአብሔርመንገድ ይዘምሩ።

6 እግዚአብሔርበከፍታ ስፍራ ቢሆንም፣ ዝቅ ያለውን ይመለከተዋል፤

ትዕቢተኛውን ከሩቅ ያውቀዋል።

7 በመከራ መካከል ብሄድም፣

አንተ ሕይወቴን ትጠብቃታለህ፤

በጠላቶቼ ቍጣ ላይ እጅህን ትዘረጋለህ፤

በቀኝ እጅህም ታድነኛለህ።

8 እግዚአብሔርበእኔ ላይ ያለውን ዐላማ ይፈጽማል፤

እግዚአብሔርሆይ፤ ምሕረትህ ለዘላለም ነው።

የእጅህንም ሥራ ቸል አትበል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *