የሚታደን ሰው ጸሎት
ዋሻ ውስጥ በነበረ ጊዜ፤ የዳዊት ትምህርት፤
ጸሎት
1 ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደእግዚአብሔርእጮኻለሁ፤
ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደእግዚአብሔርልመና አቀርባለሁ።
2 ብሶቴን በፊቱ አፈስሳለሁ፤
ችግሬንም በፊቱ እናገራለሁ።
3 መንፈሴ በውስጤ ሲዝል፣
መንገዴን የምታውቅ አንተ ነህ፤
በመተላለፊያ መንገዴ ላይ፤
ወጥመድ በስውር ዘርግተውብኛል።
4 ወደ ቀኜ ተመልከት፤ እይም፤
ስለ እኔ የሚገደው የለም፤
ማምለጫም የለኝም፤
ስለ ነፍሴም ደንታ ያለው የለም።
5 እግዚአብሔርሆይ፤ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤
ደግሞም፣ “አንተ መጠጊያዬ ነህ፤
በሕያዋንም ምድር ዕድል ፈንታዬ ነህ” እላለሁ።
6 እጅግ ተስፋ ቈርጫለሁና፣
ጩኸቴን ስማ፤
ከዐቅም በላይ ሆነውብኛልና፣
ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።
7 ስምህን አመሰግን ዘንድ፣ ነፍሴን ከወህኒ አውጣት፤
ከምታደርግልኝም በጎ ነገር የተነሣ፣
ጻድቃን በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ።