መዝሙር 145

ምስጋና ለንጉሡ ለእግዚአብሔር

የዳዊት የምስጋና መዝሙር

1 አምላኬና ንጉሤ ሆይ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤

ስምህን ከዘላለም እስከ ዘላለም እባርካለሁ።

2 በየቀኑ እባርክሃለሁ፤

ስምህንም ከዘላለም እስከ ዘላለም አመሰግናለሁ።

3 እግዚአብሔርታላቅ ነው፤ እጅግ ሊመሰገንም ይገባዋል፤

ታላቅነቱም አይመረመርም።

4 ሥራህን አንዱ ትውልድ ለሌላው ትውልድ ያስተጋባል፤

ብርቱ ሥራህን ያውጃል።

5 ስለ ግርማህ ውበትና ክብር ይናገራሉ፤

ስለ ድንቅ ሥራህምያወራሉ።

6 ስለ ድንቅ ሥራህ ብርታት ይነጋገራሉ፤

እኔም ስለ ታላቅነትህ ዐውጃለሁ።

7 የበጎነትህን ብዛት በደስታ ያወሳሉ፤

ስለ ጽድቅህም በእልልታ ይዘምራሉ።

8 እግዚአብሔርቸር ነው፤ ርኅሩኅም ነው፤

ለቍጣ የዘገየ፣ ምሕረቱ የበዛ።

9 እግዚአብሔርለሁሉ ቸር ነው፤

ምሕረቱም በፍጥረቱ ሁሉ ላይ ነው።

10 እግዚአብሔርሆይ፤ ፍጥረትህ ሁሉ ያመሰግንሃል፤

ቅዱሳንህም ይባርኩሃል።

11 ስለ መንግሥትህ ክብር ይናገራሉ፤

ስለ ኀይልህም ይነጋገራሉ፤

12 በዚህም ብርቱ ሥራህን፣

የመንግሥትህንም ግርማ ክብር ያስታውቃሉ።

13 መንግሥትህ የዘላለም መንግሥት ናት፤

ግዛትህም ለትውልድ ሁሉ ጸንቶ ይኖራል።

እግዚአብሔርቃሉን ሁሉ ይጠብቃል፤

በሥራውምሁሉ ቸር ነው።

14 እግዚአብሔርየሚንገዳገዱትን ሁሉ ይደግፋል፤

የወደቁትንም ሁሉ ያነሣል።

15 የሁሉ ዐይን አንተን በተስፋ ይጠብቃል፤

አንተም ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸዋለህ።

16 አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤

የሕያዋን ፍጥረታትንም ሁሉ ፍላጎት ታረካለህ።

17 እግዚአብሔርበመንገዱ ሁሉ ጻድቅ፣

በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።

18 እግዚአብሔርለሚጠሩት ሁሉ፣

በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።

19 ለሚፈሩት ፍላጎታቸውን ይፈጽማል፤

ጩኸታቸውን ይሰማል፤ ያድናቸዋልም።

20 እግዚአብሔርየሚወዱትን ሁሉ ይጠብቃል፤

ክፉዎችን ሁሉ ግን ያጠፋል።

21 አፌየእግዚአብሔርንምስጋና ይናገራል፤

ፍጡር ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ ቅዱስ ስሙን ይባርክ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *