ለረድኤት አምላክ ምስጋና
1 ሃሌ ሉያ።
ነፍሴ ሆይ፤እግዚአብሔርንባርኪ።
2 በምኖርበት ዘመን ሁሉእግዚአብሔርን
አመሰግናለሁ፤
በሕይወትም እስካለሁ ለአምላኬ እዘምራለሁ።
3 በገዦች አትታመኑ፤ ማዳን በማይችሉ ሥጋ ለባሾችም አትመኩ።
4 መንፈሳቸው ትወጣለች፤ ወደ መሬታቸውም ይመለሳሉ፤
ያን ጊዜም ዕቅዳቸው እንዳልነበር ይሆናል።
5 ረዳቱ የያዕቆብ አምላክ የሆነ፣
ተስፋውንም በአምላኩበእግዚአብሔርላይ የጣለ ሰው ምስጉን ነው፤
6 እርሱ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም፣
በእነዚህም ውስጥ ያለውን ሁሉ የፈጠረ፣
ታማኝነቱንም ለዘላለም የሚጠብቅ ነው፤
7 ለተበደሉት የሚፈርድ፣
ለተራቡት ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፤
እግዚአብሔርእስረኞችን ከእስራት ያወጣል፤
8 እግዚአብሔርየዕዉራንን ዐይን ያበራል፤
እግዚአብሔርየተዋረዱትን ከፍ ያደርጋል፤
እግዚአብሔርጻድቃንን ይወዳል፤
9 እግዚአብሔርስደተኞችን ይጠብቃል፤
ድኻ ዐደጎችንና መበለቶችን ይደግፋል፤
የክፉዎችን መንገድ ግን ያጠፋል።
10 እግዚአብሔርለዘላለም ይነግሣል፤
ጽዮን ሆይ፤ አምላክሽ ለትውልድ ሁሉ ንጉሥ ነው።
ሃሌ ሉያ።