የምስጋና መዝሙር
1 ሃሌ ሉያ።
እግዚአብሔርንበመቅደሱ አመስግኑት፤
በታላቅ ጠፈሩ አወድሱት።
2 ስለ ብርቱ ሥራው አመስግኑት፤
እጅግ ታላቅ ነውና ወድሱት።
3 በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤
በበገናና በመሰንቆ ወድሱት።
4 በከበሮና በሽብሸባ አመስግኑት፤
በባለ አውታር መሣሪያና በእምቢልታ አወድሱት።
5 ተርገብጋቢ ድምፅ ባለው ጸናጽል አመስግኑት፤
ድምፀ መልካም በሆነ ጸናጽል ወድሱት።
6 እስትንፋስ ያለው ሁሉእግዚእብሔርንያመስግን።
ሃሌ ሉያ።