መዝሙር 16

እግዚአብሔር ርስቴ

የዳዊት ቅኔ

1 አምላክ ሆይ፤ መጠጊያዬ ነህና፣

በከለላህ ሰውረኝ።

2 እግዚአብሔርን፣ ‘አንተ ጌታዬ ነህ፤

ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም”

አልሁት።

3 በምድር ያሉ ቅዱሳን፣

ሙሉ ደስታ የማገኝባቸው ክቡራን ናቸው።

4 ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ፣

ሐዘናቸው ይበዛል፤

እኔ ግን የደም ቍርባናቸውን አላፈስም፤

ስማቸውንም በአፌ አልጠራም፤

5 እግዚአብሔርየርስት ድርሻዬና ጽዋዬ ነው፤

ዕጣዬም በእጅህ ናት።

6 መካለያ ገመድ ባማረ ስፍራ ተጥሎልኛል፤

በርግጥም የተዋበች ርስት አግኝቻለሁ።

7 የሚመክረኝንእግዚአብሔርንእባርካለሁ፤

በሌሊት እንኳ ልቤ ቀናውን ያመላክተኛል።

8 እግዚአብሔርንሁል ጊዜ በፊቴ አድርጌአለሁ፤

እርሱ በቀኜ ስላለ አልናወጥም።

9 ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ ነፍሴም ሐሤት አደረገች፤

ሥጋዬም ያለ ሥጋት ዐርፎ ይቀመጣል፤

10 በሲኦልውስጥ አትተወኝምና፤

ቅዱስህምመበስበስን እንዲያይ አታደርግም።

11 የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤

በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣

በቀኝህም የዘላለም ፍሥሓ አለ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *