የድል መዝሙር
ለመዘምራን አለቃ፤
የእግዚአብሔ
ር ባሪያ የዳዊት መዝሙር፤ ይህም
እግዚአብሔር
ከሳዖልና ከጠላቶቹ ሁሉ እጅ በታደገው ጊዜ፣
ለእግዚአብሔር
እንዲህ ሲል የዘመረው ነው፦
1 ጒልበቴእግዚአብሔርሆይ፤ እወድሃለሁ።
2 እግዚአብሔርዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፤
አምላኬ የምሸሸግበት ዐለቴ፤
እርሱ ጋሻዬ፣ የድነቴ ቀንድናዐምባዬ ነው።
3 ምስጋና የሚገባውንእግዚአብሔርንእጠራለሁ፤
ከጠላቶቼም እድናለሁ።
4 የሞት ገመድ አነቀኝ፤
የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ።
5 የሲኦልገመድ ተጠመጠመብኝ፤
የሞት ወጥመድም ተጋረጠብኝ።
6 በተጨነቅሁ ጊዜእግዚአብሔርንጠራሁት፤
እንዲረዳኝም ወደ አምላኬ ጮኽሁ፤
እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤
ጩኸቴም ከፊቱ ደረሰ፤ ወደ ጆሮውም ገባ።
7 ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤
የተራሮችም መሠረት ተናጋ፤
ጌታ ተቈጥቶአልና ተንቀጠቀጡ።
8 ከአፍንጫው ጢስ ወጣ፤
የሚባላ እሳት ከአፉ፤
የፍም ነበልባል ከእርሱ ፈለቀ።
9 ሰማያትን ሰንጥቆ ወረደ፤
ከእግሩም በታች ጥቍር ደመና ነበረ።
10 በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤
በነፋስም ክንፍ መጠቀ።
11 ጨለማን መሰወሪያው፣ በዙሪያውም አጐበሩ አደረገው፤
በዝናብ አዘል ጥቍር ደመናም ተሸፈነ።
12 በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ፣
ደመናት፣ የበረዶ ድንጋይና መብረቅ ወጡ።
13 እግዚአብሔርከሰማያት አንጐደጐደ፤
ልዑልም ድምፁን አስተጋባ።
14 ፍላጻውን አስፈንጥሮ በተናቸው፤
መብረቅ አዥጐድጒዶ አሳደዳቸው።
15 እግዚአብሔርሆይ፤ ከተግሣጽህ የተነሣ፣
ከአፍንጫህም እስትንፋስ የተነሣ፣
የባሕር ወለል ተገለጠ፤
የዓለምም መሠረት ራቍቱን ቀረ።
16 ከላይ እጁን ወደ ታች ዘርግቶ ያዘኝ፤
ከብዙ ጥልቅ ውሃም አወጣኝ፤
17 ከኀያላን ጠላቶቼ አዳነኝ፤
ከእኔ ከሚበረቱ ባላንጣዎቼም ታደገኝ።
18 እነርሱ በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤
እግዚአብሔርግን ድጋፍ ሆነኝ።
19 ወደ ሰፊ ስፍራ አወጣኝ፤
ደስ ተሰኝቶብኛልና አዳነኝ።
20 እግዚአብሔርእንደ ጽድቄ መልሶልኛል፤
እንደ እጄ ንጽሕናም ከፍሎኛል፤
21 የእግዚአብሔርንመንገድ ጠብቄአለሁና፤
አምላኬንም በመተው ክፉ አላደረግሁም።
22 ሕጎቹ ሁሉ በፊቴ ናቸው፤
ሥርዐቱን ከፊቴ አላራቅሁም።
23 በፊቱ ነቀፋ አልነበረብኝም፤
ራሴንም ከኀጢአት ጠብቄአለሁ።
24 እግዚአብሔርእንደ ጽድቄ መጠን፣
በፊቱም እንደ እጄም ንጽሕና ከፍሎኛል።
25 ከታማኙ ጋር ታማኝ ትሆናለህ፤
እንከን ከሌለበት ጋር ያለ እንከን ትሆናለህ፤
26 ከንጹሑ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤
ለጠማማው አንተ ትጠምበታለህ።
27 አንተ ትሑታንን ታድናለህ፤
ትዕቢተኛውን ዐይን ግን ታዋርዳለህ።
28 እግዚአብሔርሆይ፤ አንተ መብራቴን ታበራለህ፤
አምላኬ ሆይ፤ ጨለማዬን ብርሃን ታደርገዋለህ።
29 በአንተ ጒልበት በሰራዊት ላይ እረማመዳለሁ፤
በአምላኬም ኀይል ቅጥር እዘላለሁ።
30 የአምላክ መንገድ ፍጹም ነው፤
የእግዚአብሔርቃል የነጠረ ነው።
መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ፣
እርሱ ጋሻ ነው።
31 ከእግዚአብሔርበቀር ማን አምላክ አለ?
ከአምላካችንስ በቀር ዐምባ ማን ነው?
32 ኀይልን የሚያስታጥቀኝ፣
መንገዴንም የሚያቃና እግዚአብሔር ነው።
33 እርሱ እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች ያደርጋል፤
በከፍታዎችም ላይ ያቆመኛል።
34 እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናቸዋል፤
ክንዴም የናስ ቀስት መገተር ይችላል።
35 የድል ጋሻ ሰጥተኸኛል፤
ቀኝ እጅህም ደግፋ ይዛኛለች፤
ዝቅ ብለህም ከፍ አደረግኸኝ።
36 ከሥሬ ያለውን ስፍራ ለአረማመዴ አሰፋህልኝ፤
እግሬም አልተንሸራተተም።
37 ጠላቶቼን አሳድጄ ያዝኋቸው፤
እስኪጠፉም ወደ ኋላዬ አልተመለስሁም።
38 እንዳያንሰራሩ አድርጌ አደቀቅኋቸው፤
ከእግሬም ሥር ወደቁ።
39 አንተ ለጦርነት ኀይልን አስታጠቅኸኝ፤
ባላንጦቼ እግሬ ላይ እንዲደፉ አደረግህ።
40 ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው እንዲሸሹ አደረግህ፤
እኔም የሚጠሉኝን አጠፋኋቸው።
41 ለርዳታ ጮኹ፤ የሚያስጥላቸው ግን አላገኙም፤
ወደእግዚአብሔርጮኹ፤ እርሱም አልመለሰላቸውም።
42 ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ አደቀቅኋቸው፤
እንደ መንገድ ላይ ጭቃም አውጥቼ ጣልኋቸው።
43 ከሕዝብ ግርግር አወጣኸኝ፤
የሕዝቦች መሪ አድርገህ አስቀመጥኸኝ፤
የማላውቀውም ሕዝብ ተገዛልኝ።
44 ትእዛዜን እንደ ሰሙ ይታዘዙልኛል፤
ባዕዳንም በፊቴ አንገት ደፉ።
45 ባዕዳን በፍርሃት ተዋጡ፤
ከምሽጋቸውም እየተንቀጠቀጡ ወጡ።
46 እግዚአብሔርሕያው ነው! ዐምባዬ ይባረክ፤
ያዳነኝ አምላክ ከፍ ከፍ ይበል።
47 እርሱ በቀሌን የሚመልስልኝ፣
ሕዝቦችንም የሚያስገዛልኝ አምላክ ነው፤
48 ከጠላቶቼም የሚታደገኝ እርሱ ነው።
አንተ ከባላንጦቼ በላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤
ከጨካኞች አዳንኸኝ።
49 እግዚአብሔርሆይ፤ ስለዚህ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤
ስምህንም በመዝሙር እወድሳለሁ።
50 እርሱ ላነገሠው ታላላቅ ድሎችን ይሰጣል፤
ጽኑ ፍቅሩንም ለቀባው፣
ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም ይገልጣል።