መልካሙ እረኛ
የዳዊት መዝሙር
1 እግዚአብሔርእረኛዬ ነው፤
አንዳች አይጐድልብኝም።
2 በለመለመ መስክ ያሳርፈኛል፤
በዕረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል፤
3 ነፍሴንም ይመልሳታል።
ስለ ስሙም፣
በጽድቅ መንገድ ይመራኛል።
4 በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ፤
ብሄድ እንኳ፣
አንተ ከእኔ ጋር ስለ ሆንህ፣
ክፉን አልፈራም፤
በትርህና ምርኵዝህ፣
እነርሱ ያጽናኑኛል።
5 ጠላቶቼ እያዩ፣
በፊቴ ማዕድ አዘጋጀህልኝ፤
ራሴን በዘይት ቀባህ፤
ጽዋዬም ሞልቶ ይፈስሳል።
6 በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣
በጎነትና ምሕረት በእርግጥ ይከተሉኛል፤
እኔምበእግዚአብሔርቤት፣
ለዘላለም እኖራለሁ።