ወደ መቅደስ መግቢያ ጸሎት
የዳዊት መዝሙር
1 ምድርና በእርሷ ያለው ሁሉ፣
ዓለምና በውስጧ የሚኖር ሁሉየእግዚአብሔርነው፤
2 እርሱ በባሕሮች ላይ መሥርቶአታልና፤
በውሆችም ላይ አጽንቶአታል።
3 ወደእግዚአብሔርተራራ ማን ሊወጣ ይችላል?
በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል?
4 ንጹሕ እጅና ቅን ልብ ያለው፤
ነፍሱን ለሐሰት ነገር የማያስገዛ፤
በውሸት የማይምል፤
5 እርሱ በረከትንከእግዚአብሔርዘንድ፣
ምሕረትንም ከአዳኝ አምላኩ ይቀበላል።
6 እርሱን የሚፈልግ ትውልድ እንዲህ ነው፤
የያዕቆብ አምላክ ሆይ፤ ፊትህንየሚፈልግ እንዲህ ያለ ነው።ሴላ
7 እናንተ ደጆች፤ ቀና በሉ፤
እናንተ የዘላለም በሮች፤
የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!
8 ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?
እግዚአብሔርነው ብርቱና ኀያል፤
እግዚአብሔርነው በውጊያ ኀያል።
9 እናንተ ደጆች፤ ቀና በሉ፤
እናንተ የዘላለም በሮች፤
የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!
10 ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?
የሰራዊትአምላክ፣
እርሱ የክብር ንጉሥ ነው።ሴላ