በአደጋ ጊዜ የቀረበ ጸሎት
የዳዊት መዝሙር
1 እግዚአብሔርሆይ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁ፤
2 አምላኬ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ፤
እባክህ አታሳፍረኝ፤
ጠላቶቼም አይዘባነኑብኝ።
3 አንተን ተስፋ የሚያደርጉ፣
ከቶ አያፍሩም፤
ነገር ግን እንዲያው ያለ ምክንያት፣
ተንኰለኞች የሆኑ ያፍራሉ።
4 እግዚአብሔርሆይ፤ አካሄድህን እንዳውቅ አድርገኝ፤
መንገድህንም አስተምረኝ።
5 አንተ አዳኜ፣ አምላኬም ነህና፣
በእውነትህ ምራኝ፤ አስተምረኝም፤
ቀኑን ሙሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።
6 እግዚአብሔርሆይ፤ ምሕረትህንና ፍቅርህን አስብ፤
እነዚህ ከጥንት የነበሩ ናቸውና።
7 የልጅነቴን ኀጢአት፣
መተላለፌንም አታስብብኝ፤
እግዚአብሔርሆይ፤ እንደ ቸርነትህ ብዛት፣
እንደ ምሕረትህም መጠን ዐስበኝ።
8 እግዚአብሔርመልካምና ቅን ነው፤
ስለዚህ ኀጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋል።
9 ዝቅ ያሉትን በፍትሕ ይመራቸዋል፤
ለትሑታንም መንገዱን ያስተምራቸዋል።
10 ኪዳኑንና ሥርዐቱን ለሚጠብቁ፣
የእግዚአብሔርመንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ናቸው።
11 እግዚአብሔርሆይ፤ ኀጢአቴ ታላቅ ነውና፣
ስለ ስምህ ይቅር በልልኝ።
12 እግዚአብሔርንየሚፈራ ሰው ማን ነው?
በተመረጠለት መንገድ ያስተምረዋል።
13 ዘመኑን በተድላ ደስታ ያሳልፋል፤
ዘሩም ምድርን ይወርሳል።
14 እግዚአብሔርምስጢሩን ከሚፈሩት ወዳጆቹ አይሰውርም፤
ኪዳኑንም ይገልጥላቸዋል።
15 ዐይኖቼ ሁል ጊዜ ወደእግዚአብሔርናቸው፤
እግሮቼን ከወጥመድ የሚያላቅቃቸው እርሱ ነውና።
16 እኔ ብቸኛና የተጨነቅሁ እንደ መሆኔ፣
ወደ እኔ ተመለስ፤ ምሕረትም አድርግልኝ።
17 የልቤ መከራ በዝቶአል፤
ከጭንቀቴ ገላግለኝ።
18 ጭንቀቴንና መከራዬን ተመልከት፤
ኀጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።
19 ጠላቶቼ እንዴት እንደ በዙ ተመልከት፤
እንዴት አምርረው እንደሚጠሉኝ እይ።
20 ነፍሴን ጠብቃት፤ ታደገኝም፤
መጠጊያዬ ነህና አታሳፍረኝ።
21 አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና፣
ታማኝነትና ቅንነት ይጠብቁኝ።
22 አምላክ ሆይ፤ እስራኤልን፣
ከመከራው ሁሉ አድነው።