መዝሙር 27

ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ሰው ድፍረት

የዳዊት መዝሙር

1 እግዚአብሔርብርሃኔና መድኅኔ ነው፤

የሚያስፈራኝ ማን ነው?

እግዚአብሔርለሕይወቴ ዐምባዋ ነው፤

ማንን እፈራለሁ?

2 ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ፣

ክፉዎች ገፍተው በመጡ ጊዜ፣

ጠላቶቼና ባላጋራዎቼ በተነሡብኝ ጊዜ፣

እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ።

3 ሰራዊት ቢከበኝ እንኳ፣

ልቤ አይፈራም፤

ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ፣

ልበ ሙሉ ነኝ።

4 እግዚአብሔርንአንዲት ነገር እለምነዋለሁ፤

እርሷንም እሻለሁ፤

ይኸውም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣

በእግዚአብሔርቤት እኖር ዘንድ፣

የእግዚአብሔርንክብር ውበት አይ ዘንድ፣

በመቅደሱም ሆኜ አሰላስል ዘንድ ነው።

5 በመከራ ቀን፣

በድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛልና፤

በድንኳኑም ጓዳ ይሸሽገኛል፤

6 በዚህ ጊዜ በዙሪያዬ ባሉ ጠላቶቼ ላይ፣

ራሴ ከፍ ከፍ ይላል፤

በድንኳኑም ውስጥ የእልልታ መሥዋዕት እሠዋለሁ፤

ለእግዚአብሔርእቀኛለሁ፤

እዘምርለታለሁም።

7 እግዚአብሔርሆይ፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ስማኝ፤

ራራልኝ፤ ስማኝም።

8 “ፊቴን ፈልጉ” ባልህ ጊዜ፤

ልቤእግዚአብሔርሆይ፤ ፊትህን እሻለሁ አለች።

9 ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤

ተቈጥተህ አገልጋይህን አታርቀው፤

መቼም ረዳቴ ነህና።

አዳኝ አምላኬ ሆይ፤

አትጣለኝ፤ አትተወኝም።

10 አባቴና እናቴ ቢተዉኝ እንኳ፣

እግዚአብሔርይቀበለኛል።

11 እግዚአብሔርሆይ፤ መንገድህን አስተምረኝ፤

ስለ ጠላቶቼም፣

በቀና መንገድ ምራኝ።

12 ለጠላቶቼ ፍላጎት አሳልፈህ አትስጠኝ፤

የሐሰት ምስክሮች ተነሥተውብኛልና፣

ዐመፃ የሚረጩ ናቸው።

13 የእግዚአብሔርንቸርነት፣

በሕያዋን ምድር እንደማይ፣

ሙሉ እምነቴ ነው።

14 እግዚአብሔርንተስፋ አድርግ፤

አይዞህ፣ በርታ፤

እግዚአብሔርንተስፋ አድርግ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *