ለማዕበሉ ጌታ የቀረበ ውዳሴ
የዳዊት መዝሙር
1 እናንተ ኀያላን፣ለእግዚአብሔርስጡ፤
ክብርንና ብርታትንለእግዚአብሔርስጡ።
2 ለስሙ የሚገባ ክብርለእግዚአብሔርስጡ፤
በቅድስናው ግርማለእግዚአብሔርስገዱ።
3 የእግዚአብሔርድምፅ በውሆች ላይ ነው፤
የክብር አምላክ አንጐደጐደ፤
እግዚአብሔርበታላላቅ ውሆች ላይ አንጐደጐደ።
4 የእግዚአብሔርድምፅ ኀያል ነው፤
የእግዚአብሔርድምፅ ግርማዊ ነው።
5 የእግዚአብሔርድምፅ ዝግባን ይሰብራል፤
እግዚአብሔርየሊባኖስን ዝግባ ይሰባብራል።
6 ሊባኖስን እንደ ጥጃ፣
ስርዮንንምእንደ አውራሪስ ግልገል ያዘልላል።
7 የእግዚአብሔርድምፅ
የእሳት ነበልባል ይረጫል።
8 የእግዚአብሔርድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፤
የእግዚአብሔርድምፅ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።
9 የእግዚአብሔርድምፅ ወርካዎችን ይወዘውዛል፤
ጫካዎችንም ይመነጥራል፤
ሁሉም በእርሱ ቤተ መቅደስ ሆኖ “ይክበር!” ይላል።
10 እግዚአብሔርበጐርፍ ላይ ዙፋኑን ዘርግቶ ተቀምጦአል፤
እግዚአብሔርበንጉሥነቱ ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።
11 እግዚአብሔርለሕዝቡ ብርታትን ይሰጣል፤
እግዚአብሔርሕዝቡን በሰላም ይባርካል።