መዝሙር 33

ውዳሴ ለቸር አምላክ

1 ጻድቃን ሆይ፤በእግዚአብሔርደስ ይበላችሁ፤

ቅኖች ሊወድሱት ይገባቸዋል።

2 እግዚአብሔርንበመሰንቆ አመስግኑት፤

ዐሥር አውታር ባለውም በገና ዘምሩለት።

3 አዲስ መዝሙር ዘምሩለት፤

በገናውን ባማረ ቅኝት ደርድሩ፤ እልልም በሉ።

4 የእግዚአብሔርቃል እውነት ነውና፤

የሚሠራውም ሁሉ የታመነ ነው።

5 እርሱ ጽድቅንና ፍትሕን ይወዳል፤

ምድርም በምሕረቱ የተሞላች ናት።

6 በእግዚአብሔርቃል ሰማያት ተሠሩ፤

በአፉም እስትንፋስ የከዋክብት ሰራዊት።

7 የባሕርን ውሃ በአንድ ዕቃ ይሰበስባል፤

ቀላዩንም በአንድ ስፍራ ያከማቻል።

8 ምድር ሁሉእግዚአብሔርንትፍራው፤

በዓለም የሚኖር ሕዝብ ሁሉ በፊቱ ይንቀጥቀጥ።

9 እርሱ ተናግሮአልና ሆኑ፤

አዞአልና ጸኑም።

10 እግዚአብሔርየሕዝቦችን ምክክር ከንቱ ያደርጋል፤

የሕዝብንም ዕቅድ ያጨናግፋል።

11 የእግዚአብሔርሐሳብ ግን ለዘላለም ይጸናል፤

የልቡም ሐሳብ ለትውልድ ሁሉ ነው።

12 እግዚአብሔርአምላኩ የሆነው ሕዝብ፣

ለርስቱ የመረጠውም ወገን የተባረከ ነው።

13 እግዚአብሔርከሰማይ ይመለከታል፤

የሰውንም ልጆች ሁሉ ያያል፤

14 ከማደሪያው ቦታ ሆኖ፣

በምድር ወደሚኖሩት ሁሉ ይመለከታል፤

15 እርሱ የሁሉን ልብ የሠራ፣

የሚያደርጉትን ሁሉ የሚያስተውል ነው።

16 ንጉሥ በሰራዊቱ ታላቅነት አይድንም፤

ጀግናም በኀይሉ ብርታት አያመልጥም።

17 በፈረስ ድል አደርጋለሁ ማለት ከንቱ ተስፋ ነው፤

በብርቱ ጒልበቱም ማንንም አያድንም።

18 እነሆ፤የእግዚአብሔርዐይኖች በሚፈሩት ላይ ናቸው፤

ምሕረቱንም በሚጠባበቁት ላይ አትኵረዋል።

19 በዚህም ነፍሳቸውን ከሞት ያድናል፤

በራብ ዘመንም በሕይወት ያኖራቸዋል።

20 ነፍሳችንእግዚአብሔርንተስፋ ታደርጋለች፤

እርሱ ረዳታችንና መጠጊያችን ነው።

21 ልባችን በእርሱ ደስ ይለዋል፤

በቅዱስ ስሙ ታምነናልና።

22 እግዚአብሔርሆይ፤ ተስፋ ባደረግንህ፣

በእኛ ላይ ምሕረትህ ትሁን።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *