መዝሙር 46

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር

ለመዘምራን አለቃ፤ የቆሬ ልጆች መዝሙር፤ በደናግል የዜማ ስልት የሚዘመር፣ መዝሙር።

1 አምላካችን መጠጊያችንና ኀይላችን፣

በሚደርስብን መከራ ሁሉ የቅርብ ረዳታችን ነው።

2 ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ እንኳ፣

ተራሮችም ወደ ባሕር ጥልቅ ቢሰምጡ አንፈራም።

3 ውሆች ቢያስገመግሙ፣ ዐረፋ ቢደፍቁም፣ ተራሮችም ከውሆቹ ሙላት የተነሣ

ቢንቀጠቀጡም አንደናገጥም።ሴላ

4 የእግዚአብሔርን ከተማ፣

የልዑልን የተቀደሰ ማደሪያ ደስ የሚያሰኝ የወንዝ ፈሳሾች አሉ።

5 እግዚአብሔር በመካከሏ ነው፤ አትናወጥም፤

አምላክ በማለዳ ይረዳታል።

6 ሕዝቦች በዐመፅ ተነሡ፤ መንግሥታትም ወደቁ፤

ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰማ፤ ምድርም ቀለጠች።

7 የሰራዊትአምላክከእኛ ጋር ነው፤

የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።ሴላ

8 ኑናየእግዚአብሔርንሥራ፣

ምድርንም እንዴት ባድማ እንዳደረጋት እዩ።

9 ከዳር እስከ ዳር ጦርነትን ከምድር ያስወግዳል፤

ቀስትን ይሰብራል፤ ጦርን ያነክታል፤

ጋሻንምበእሳት ያቃጥላል።

10 “ዕረፉ፤ እኔም አምላክ እንደሆንሁ ዕወቁ፤

በሕዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፤

በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”

11 የሰራዊትአምላክከእኛ ጋር ነው፤

የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።ሴላ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *