የጭንቀት ጩኸት
ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር፤ ለመታሰቢያ
1 አምላክ ሆይ፤ ታድነኝ ዘንድ ዘንበል በል፤
እግዚአብሔርሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
2 ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ፣
ይፈሩ፤ ሁከትም ይምጣባቸው፤ የእኔን መጐዳት የሚመኙ፣
በውርደት ወደ ኋላቸው ይመለሱ።
3 በእኔ ላይ፣ “እሰይ! እሰይ!” የሚሉ፣
ተሸማቀው ወደ ኋላ ይመለሱ።
4 ነገር ግን የሚሹህ ሁሉ፣
በአንተ ሐሤት ያድርጉ፤ ደስም ይበላቸው፤
“ማዳንህን የሚወዱ ሁሉ ሁል ጊዜ፣
እግዚአብሔር ከፍ ይበል!” ይበሉ።
5 እኔ ግን ምስኪንና ችግረኛ ነኝ፤
አምላክ ሆይ፤ ፈጥነህ ድረስልኝ፤
ረዳቴም፣ ታዳጊዬም አንተ ነህና፤
እግዚአብሔርሆይ፤ አትዘግይ።