መዝሙር 85

ለሰላም የቀረበ ጸሎት

ለመዘምራን አለቃ፤ የቆሬ ልጆች፤ መዝሙር

1 እግዚአብሔርሆይ፤ ለምድርህ በጎ ውለሃል፤

የያዕቆብንም ምርኮ መለስህ።

2 የሕዝብህን በደል ይቅር አልህ፤

ኀጢአታቸውንም ሁሉ ሸፈንህ።ሴላ

3 መዓትህን ሁሉ አራቅህ፤

ከብርቱ ቍጣህም ተመለስህ።

4 መድኀኒታችን የሆንህ አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤

በእኛ ላይ የተቃጣውን ቍጣህን መልሰው።

5 የምትቈጣን ለዘላለም ነውን?

ቊጣህስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይቀጥላልን?

6 ሕዝብህ በአንተ ሐሤት ያደርግ ዘንድ፣

መልሰህ ሕያዋን አታደርገንምን?

7 እግዚአብሔርሆይ፤ ምሕረትህን አሳየን፤

ማዳንህን ለግሰን።

8 እግዚአብሔርአምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ፤

ለሕዝቡ፣ ለቅዱሳኑ ሰላምን ይናገራልና፤

ዳሩ ግን ወደ ከንቱ ምግባራቸው አይመለሱ።

9 ክብሩ በምድራችን ይኖር ዘንድ፣

ማዳኑ ለሚፈሩት በእርግጥ ቅርብ ነው።

10 ምሕረትና ታማኝነት ተገናኙ፤

ጽድቅና ሰላም ተቃቀፉ።

11 ታማኝነት ከምድር በቀለች፤

ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተች።

12 እግዚአብሔርበጎ ነገር ይለግሳል፤ ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች።

13 ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፤

ለአረማመዱም መንገድ ያዘጋጃል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *