ጽዮን የሕዝቦች እናት
የቆሬ ልጆች መዝሙር፤ ማሕሌት
1 መሠረቱን በተቀደሱ ተራሮች አቆመ፤
2 እግዚአብሔርከያዕቆብ ማደሪያዎች ሁሉ ይልቅ፣
የጽዮንን ደጆች ይወዳል።
3 የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፤
ስለ አንቺ ክቡር የሆነ ነገር እንዲህ ተብሎ ይነገራል፤ሴላ
4 “ከሚያውቁኝ መካከል፣
ረዓብንናባቢሎንን እጠቅሳለሁ፤
እነሆ፤ ፍልስጥኤምና ጢሮስ ከኢትዮጵያ ጋር፣
‘ይህሰው በዚያ ነው የተወለደው’ ይላሉ።”
5 በእርግጥም ስለ ጽዮን፣
“ይህም ያም ሰው በእርሷ ውስጥ ተወለዱ፤
ልዑልም ራሱ ያጸናታል” ይባላል።
6 እግዚአብሔርሕዝቡን ሲመዘግብ፣
“ይህ ሰው የተወለደው በዚያ ነው” ብሎ ይጽፋል።ሴላ
7 የሚያዜሙም መሣሪያ የሚጫወቱም፣
“ምንጩ ሁሉ በአንቺ ውስጥ ይገኛል” ይላሉ።