መዝሙር 88

ሰቆቃ

ማሕሌት፤ የቆሬ ልጆች መዝሙር፤ ለመዘምራን አለቃ፤ በማኸላት የሚዘመር፤ የይዝራኤላዊው የኤማን ትምህርት

1 አዳኜ የሆንህ አምላክእግዚአብሔርሆይ፤

በቀንና በሌሊት በፊትህ አጮኻለሁ።

2 ጸሎቴ በፊትህ ትድረስ፤

ጆሮህንም ወደ ጩኸቴ አዘንብል፤

3 ነፍሴ በመከራ ተሞልታለችና፤

ሕይወቴም ወደ ሲኦልተቃርባለች።

4 ወደ ጒድጓድ ከሚወርዱት ጋር ተቈጠርሁ፤

ዐቅምም አጣሁ።

5 በሙታን መካከል እንደ ተጣሉ፣

ተገድለው በመቃብር ውስጥ እንደ ተጋደሙ፣

አንተ ከእንግዲህ እንደማታስባቸው፣

ከእጅህም ወጥተው እንደ ተወገዱ ሆንሁ።

6 በዐዘቅት ጥልቀት ውስጥ ጣልኸኝ፤

በጨለማ ጒድጓድ ውስጥ ከተትኸኝ።

7 የቊጣህ ክብደት በላዬ ዐርፎአል፤

በማዕበልህም ሁሉ አጥለቅልቀኸኛል።ሴላ

8 የሚቀርቡኝ ባልንጀሮቼን ከእኔ አራቅህ፤

እንዲጸየፉኝም አደረግህ፤

ተከብቤአለሁ፤ ማምለጥም አልችል፤

9 ዐይኖቼም በሐዘን ፈዘዙ።

እግዚአብሔርሆይ፤ ዘወትር ወደ አንተ እጣራለሁ፤

እጆቼንም ወደ አንተ ዘረጋሁ።

10 ድንቅ ሥራህን ለሙታን ታሳያለህን?

የሙታንስ መናፍስት ተነሥተው ያመሰግኑሃልን?ሴላ

11 ምሕረትህ በመቃብር ውስጥ፣

ታማኝነትህስ እንጦርጦስይነገራልን?

12 ድንቅ ሥራህ በጨለማ ስፍራ፣

ጽድቅህስ በመረሳት ምድር ትታወቃለችን?

13 እግዚአብሔርሆይ፤ እኔ ግን ትረዳኝ ዘንድ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤

በጧትም ጸሎቴን በፊትህ አደርሳለሁ።

14 እግዚአብሔርሆይ፤ ለምን ታርቀኛለህ?

ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ?

15 እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ችግረኛና ለሞት የተቃረብሁ ነበርሁ፤

መዓትህ አሠቃየኝ፤ ግራም ተጋባሁ።

16 ቍጣህ በላዬ ላይ ተከነበለ፤

መዓትህም አጠፋኝ።

17 ቀኑን ሙሉ እንደ ጐርፍ ከበቡኝ፤

በአንድነትም ዙሪያዬን አጥረው ያዙኝ።

18 ወዳጄንና ባልንጀራዬን ከእኔ አራቅህ፤

ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *