የእግዚአብሔር ግርማ
1 እግዚአብሔርነገሠ፤ ግርማንም ተጐናጸፈ፤
እግዚአብሔርግርማን ለበሰ፤
ብርታትንም ታጠቀ፤
ዓለም እንዳትናወጥ ጸንታለች፤
ማንም አይነቀንቃትም።
2 ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፤
አንተም ከዘላለም እስከ ዘላለም አለህ።
3 እግዚአብሔርሆይ፤ ወንዞች ከፍ አደረጉ፤
ወንዞች ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ፤
ወንዞች የሚያስገመግም ማዕበላቸውን ከፍ አደረጉ።
4 ከብዙ ውሆች ድምፅ ይልቅ፣
ከባሕርም ሞገድ ይልቅ፣
ከፍ ብሎ ያለውእግዚአብሔርኀያል ነው።
5 ሥርዐትህ የጸና ነው፤
እግዚአብሔርሆይ፤ እስከ ዘላለሙ፣
ቤትህ በቅድስና ይዋባል።