እግዚአብሔር፤ ንጉሥም ዳኛም
1 ለእግዚአብሔርአዲስ ዝማሬ ዘምሩ፤
ምድር ሁሉ፤ለእግዚአብሔርዘምሩ።
2 ለእግዚአብሔርዘምሩ፤ ስሙንም ባርኩ፤
ማዳኑንም ነጋ ጠባ አውሩ።
3 ክብሩን በሕዝቦች መካከል፣
ድንቅ ሥራውንም በሰዎች ሁሉ ፊት ተናገሩ።
4 እግዚአብሔርታላቅ ነውና፤ ውዳሴም የሚገባው ነው፤
ከአማልክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ ይገባዋል።
5 የሕዝብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤
እግዚአብሔርግን ሰማያትን ሠራ።
6 ክብርና ግርማ በፊቱ ናቸው፤
ብርታትና ውበትም በመቅደሱ ውስጥ አሉ።
7 የሕዝቦች ወገኖች ሆይ፤ለእግዚአብሔርስጡ፤
ክብርንና ብርታትንለእግዚአብሔርስጡ።
8 ለስሙ የሚገባ ክብርንለእግዚአብሔርስጡ፤
ቍርባንን ይዛችሁ ወደ አደባባዩ ግቡ።
9 በተቀደሰ ውበትለእግዚአብሔርስገዱ፤
ምድር ሁሉ፤ በፊቱ ተንቀጥቀጡ።
10 በሕዝቦች መካከል፣ “እግዚአብሔርነገሠ” በሉ፤
ዓለም በጽኑ ተመሥርታለች፤ አትናወጥም፤
እርሱ ለሕዝቦች በእኩልነት ይፈርዳል።
11 ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድርም ሐሤት ታድርግ፤
ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ ያስተጋባ፤
12 መስኩና በላዩ ያለው ሁሉ ይፈንጥዝ፤
ያን ጊዜ የዱር ዛፎች ሁሉ በደስታ ይዘምራሉ፤
13 እርሱ ይመጣልናበእግዚአብሔርፊት ይዘምራሉ፤
በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል፤
በዓለም ላይ በጽድቅ፣
በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል።