መዝሙር 97

የእግዚአብሔር ድል አድራጊነት

1 እግዚአብሔርነገሠ፤ ምድር ደስ ይበላት፤

በሩቅ ያሉ የባሕር ጠረፎች ሐሤት ያድርጉ።

2 ደመናና ጥቅጥቅ ያለ ጭጋግ በዙሪያው አለ፤

ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።

3 እሳት በፊቱ ይሄዳል፤

በዙሪያው ያሉትንም ጠላቶቹን ይፈጃል።

4 መብረቁ ዓለምን አበራ፤

ምድርም አይታ ተንቀጠቀጠች።

5 ተራሮችበእግዚአብሔርፊት፣

በምድርም ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ።

6 ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፤

ሕዝቦችም ሁሉ ክብሩን ያያሉ።

7 ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ፣

በጣዖታትም የሚመኩ ሁሉ ይፈሩ፤

እናንተ አማልክት ሁሉ፤ ለእርሱ ስገዱ።

8 እግዚአብሔርሆይ፤ ስለ ፍርድህ፣

ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፤

የይሁዳም ሴት ልጆች ሐሤት አደረጉ።

9 እግዚአብሔርሆይ፤ አንተ በምድር ሁሉ ላይ ልዑል ነህና፤

ከአማልክትም ሁሉ በላይ እጅግ ከፍ ያልህ ነህ።

10 እግዚአብሔርንየምትወዱ ክፋትን ጥሉ፤

እርሱ የታማኞቹን ነፍስ ይጠብቃልና፤

ከዐመፀኞችም እጅ ይታደጋቸዋል።

11 ብርሃን ለጻድቃን፣

ሐሤትም ልባቸው ለቀና ወጣ።

12 እናንተ ጻድቃንበእግዚአብሔርደስ ይበላችሁ፤

ቅዱስ ስሙንም አመስግኑ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *