የዓለም ሁሉ ዳኛ
መዝሙር
1 ለእግዚአብሔርአዲስ ዝማሬ አቅርቡ፤
እርሱ ድንቅ ነገሮችን አድርጎአልና፤
ቀኝ እጁ፣ ቅዱስ ክንዱም፣
ማዳንን አድርገውለታል።
2 እግዚአብሔርማዳኑን አሳወቀ፤
ጽድቁንም በሕዝቦች ፊት ገለጠ።
3 ለእስራኤል ቤት ምሕረቱን፣
ታማኝነቱንም አሰበ፤
የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ፣
የአምላካችንን ማዳን አዩ።
4 ምድር ሁሉለእግዚአብሔርእልል በሉ፤
ውዳሴን አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፤
5 ለእግዚአብሔርበገና ደርድሩለት፤
በበገናና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩለት፤
6 በእንቢልታና በመለከት ድምፅ፣
በንጉሡበእግዚአብሔርፊት እልል በሉ።
7 ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ፣
ዓለምና የሚኖሩባትም ሁሉ ያስገምግሙ።
8 ወንዞች በእጃቸው ያጨብጭቡ፤
ተራሮችም በአንድነት ይዘምሩ፤
9 እነዚህበእግዚአብሔርፊት ይዘምሩ፤
እርሱ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤
በዓለም ላይ በጽድቅ፣
በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል።