ሚልክያስ 3

1 “እነሆ፤ በፊቴ መንገድ እንዲያዘጋጅ መልእክተኛዬን እልካለሁ፤ የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጣል፤ ደስ የምትሰኙበትም የቃል ኪዳኑ መልእክተኛ ይመጣል” ይላልእግዚአብሔርጸባኦት።

2 እርሱ የሚመጣበትን ቀን ማን ሊቋቋመው ይችላል? በሚገለጥበትስ ጊዜ በፊቱ መቆም የሚችል ማን ነው? እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳት ወይም እንደ ልብስ አጣቢ ሳሙና ነውና።

3 ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያነጻ ሰው ይቀመጣል፤ ሌዋውያንንም አንጽቶ እንደ ወርቅና እንደ ብር ያጠራቸዋል፤ ከዚያምእግዚአብሔርቊርባንን በጽድቅ የሚያቀርቡ ሰዎች ይኖሩታል፤

4 በዚያ ጊዜ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ቊርባን እንዳለፉት ቀናትና እንደ ቀድሞው ዘመንእግዚአብሔርንደስ የሚያሰኝ ይሆናል።

5 “ስለዚህ እኔ ለፍርድ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በመተተኞች፣ በአመንዝራዎች፣ በሐሰት በሚምሉ፣ የሠራተኞችን ደመወዝ በሚከለክሉ፣ መበለቶችንና ድኻ አደጉን በሚጨቍኑ፣ መጻተኞችን ፍትሕ በሚነፍጉ፣ እኔንም በማይፈሩት ላይ እመሰክርባቸው ዘንድ እፈጥናለሁ” ይላልእግዚአብሔርጸባኦት።

እግዚአብሔርን መስረቅ

6 “እኔእግዚአብሔርአልለወጥም፤ ስለዚህ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፤ አልጠፋችሁም።

7 ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከትእዛዛቴ ፈቀቅ ብላችኋል፤ አልጠበቃችኋቸውምም፤ ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ” ይላልእግዚአብሔርጸባኦት።

“እናንተ ግን፣ የምንመለሰው እንዴት ነው ትላላችሁ?”

8 “ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን?” እናንተ ግን ትሰርቁኛላችሁ።

“እናንተ ግን፣ ‘እንዴት እንሰርቅሃለን?’ ትላላችሁ።

“ዐሥራትና መባ ትሰርቁኛላችሁ፤

9 እናንተም፣ መላው ሕዝባችሁም ስለምትሰርቁኝ የተረገማችሁ ናችሁ።

10 በቤቴ መብል እንዲኖር፣ እኔንም በዚህ እንድትፈትኑኝ ዐሥራቱን ሁሉ ወደ ጐተራ አስገቡ፤” ይላልእግዚአብሔርጸባኦት፤ “የሰማይን መስኮት የማልከፍትላችሁ፣ የተትረፈረፈ በረከትንም ማስቀመጫ እስክታጡ ድረስ የማላፈስላችሁ ከሆነ ተመልከቱ።

11 ስለ እናንተ ተባዩን እገሥጻለሁ፤ አዝመራችሁን አይበላም፤ ዕርሻ ላይ ያለ የወይን ተክላችሁም ፍሬ አልባ አይሆንም” ይላልእግዚአብሔርጸባኦት።

12 “ከዚያም በኋላ የተድላ ምድር ስለምትሆኑ ሕዝቦች ሁሉ የተባረከ ሕዝብ ብለው ይጠሯችኋል” ይላልእግዚአብሔርጸባኦት።

13 “በእኔ ላይ የድፍረት ቃል ተናግራችኋል” ይላልእግዚአብሔር።

“እናንተ ግን፣ ‘በአንተ ላይ የተናገርነው ምንድን ነው?’ ትላላችሁ።

14 “እንዲህም ብላችኋል፤ ‘እግዚአብሔርንማገልገል ከንቱ ነው፤ እርሱ የሚፈልገውን ሁሉ በማድረግናበእግዚአብሔርጸባኦት ፊት ሐዘንተኞች ሆነን በመመላለስ ምን ተጠቀምን?

15 አሁን ግን ትዕቢተኞችን ቡሩካን እንላቸዋለን፤ ክፉ አድራጊዎች ይበለጽጋሉ፤ እግዚአብሔርን የሚፈታተኑትም ያመልጣሉ።’ ”

16 በዚያን ጊዜእግዚአብሔርንየሚፈሩ ሰዎች እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፤እግዚአብሔርአዳመጠ፤ ሰማቸውም፤እግዚአብሔርንለሚፈሩና ስሙን ለሚያከብሩ በእርሱ ፊት የመታሰቢያ መጽሐፍ ተጻፈ።

17 “እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የገዛ ገንዘቤይሆናሉ” ይላልእግዚአብሔርጸባኦት፤ “አባት የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚታደግ ሁሉ እኔም እታደጋቸዋለሁ።

18 በዚያን ጊዜም እንደ ገና በጻድቁና በኀጢአተኛው መካከል፣እግዚአብሔርንበሚያገለግለውና በማያገለግለው መካከል ያለውን ልዩነት ታያላችሁ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *