ሚልክያስ 4

የእግዚአብሔር ቀን

1 “እነሆ፤ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞች ሁሉና ክፉ አድራጊዎች በሙሉ ገለባ ይሆናሉ፤ ያ የሚመጣው ቀንም ያቃጥላቸዋል” ይላልእግዚአብሔርጸባኦት። “ሥርም ሆነ ቅርንጫፍ አያስቀርላቸውም።

2 ስሜን ለምትፈሩ ለእናንተ ግን የጽድቅ ፀሐይ በክንፎቿ ፈውስ ይዛ ትወጣለች፤ እናንተም ከጋጥ እንደ ተለቀቀ እንቦሳ እየቦረቃችሁ ትወጣላችሁ።

3 እኔ በምሠራበት ቀን ክፉዎችን ትረግጣላችሁ፤ ከእግራችሁ ጫማ በታች ዐመድ ይሆናሉ” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።

4 “ለእስራኤል ሁሉ ሕጎችና ሥርዐቶች ይሆኑ ዘንድ፣ ለአገልጋዬ ለሙሴ በኮሬብ የሰጠሁትን ሕግ አስቡ።

5 “እነሆ፤ ታላቁና የሚያስፈራውየእግዚአብሔርቀን ከመምጣቱ በፊት፣ ነቢዩ ኤልያስን እልክላችኋለሁ።

6 መጥቼ ምድርን በርግማን እንዳላጠፋ፣ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፣ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *