1 በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣውየእግዚአብሔርቃል፣ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ ይህ ነው፤
2 እናንተ አሕዛብ ሆይ፤ ሁላችሁም ስሙ፤
ምድር ሆይ፤ በውስጧም የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ፤
ጌታ ከቅዱስ መቅደሱ፣
ልዑልእግዚአብሔርበእናንተ ላይ ይመሰክርባችኋል።
በሰማርያና በኢየሩሳሌም ላይ የተላለፈ ፍርድ
3 እነሆ፤እግዚአብሔርከመኖሪያ ስፍራው ይመጣል፤
ወርዶም በምድር ከፍታዎች ላይ ይራመዳል።
4 ተራሮች ከሥሩ ይቀልጣሉ፤
ሸለቆዎችም ይሰነጠቃሉ፤
በእሳት ፊት እንዳለ ሰም፣
በገደል ላይ እንደሚወርድ ፈሳሽ ይሆናሉ።
5 ይህ ሁሉ የሚሆነው ስለ ያዕቆብ በደል፣
ስለ እስራኤልም ቤት ኀጢአት ነው።
የያዕቆብ በደል ምንድን ነው?
ሰማርያ አይደለችምን?
የይሁዳስ የኰረብታ መስገጃ ምንድን ነው?
ኢየሩሳሌም አይደለችምን?
6 “ስለዚህ ሰማርያን የፍርስራሽ ክምር፣
ወይን የሚተከልባትም ስፍራ አደርጋታለሁ፤
ድንጋዮቿን ወደ ሸለቆ አወርዳለሁ፤
መሠረቷንም ባዶ አደርጋለሁ።
7 ጣዖቶችዋ ሁሉ ይሰባበራሉ፤
ለቤተ መቅደሷ የቀረበው ገጸ በረከት በእሳት ይቃጠላል፤
ምስሎችዋን ሁሉ እደመስሳለሁ፤
ገጸ በረከቷን በዝሙት አዳሪነት እንደ ሰበሰበች ሁሉ፣
አሁንም ገጸ በረከትዋ የዝሙት አዳሪነት ዋጋ መቀበያ ይሆናል።
ልቅሶና ሐዘን
8 በዚህ ምክንያት አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይም እላለሁ፤
ባዶ እግሬንና ዕርቃኔን እሄዳለሁ፤
እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ፤
እንደ ጒጒትም አቃስታለሁ።
9 ቊስሏ የማይሽር ነውና፤
ለይሁዳ ተርፎአል፤
እስከ ሕዝቤ መግቢያ በር፣
እስከ ኢየሩሳሌም እንኳ ደርሶአል።
10 በጌትአታውሩት፤
ከቶም አታልቅሱ፤
በቤትዓፍራ፣
በትቢያ ላይ ተንከባለሉ።
11 እናንት በሻፊርየምትኖሩ፣
ዕርቃናችሁን ሆናችሁ በኀፍረት ዕለፉ፤
በጸዓናንየሚኖሩ
ከዚያ አይወጡም፤
ቤትዔጼል በሐዘን ላይ ናት፤
ለእናንተም መጠጊያ ልትሆን አትችልም።
12 ከመከራው መገላገልን በመሻት፣
በማሮትየሚኖሩ በሥቃይ
ይወራጫሉ፤
እስከ ኢየሩሳሌም በር ሳይቀር፣
ክፉ ነገርከእግዚአብሔርዘንድ መጥቶአልና።
13 እናንት በለኪሶየምትኖሩ፣
ፈረሶችን ከሠረገላው ጋር አያይዙ፤
ለጽዮን ሴት ልጅ፣
የኀጢአት መጀመሪያ እናንት ነበራችሁ፤
የእስራኤል በደል
በእናንተ ዘንድ ተገኝቶአልና።
14 ስለዚህ እናንተ ለሞሬሼትጌት፣
ማጫ ትሰጣላችሁ፤
የአክዚብከተማ፣
ለእስራኤል ነገሥታት መታለያ ትሆናለች።
15 እናንት በመሪሳየምትኖሩ
ድል አድራጊ አመጣባችኋለሁ፤
ያ የእስራኤል ክብር የሆነው
ወደ ዓዶላም ይመጣል።
16 ደስ ለምትሰኙባቸው ልጆቻችሁ፣
በሐዘን ራሳችሁን ተላጩ፤
ራሳችሁን እንደ አሞራ ራስ ተመለጡት፤
ከእናንተ በምርኮ ይወሰዳሉና።