ሚክያስ 5

ከቤተ ልሔም ገዥ እንደሚመጣ የተሰጠ ተስፋ

1 አንቺ የጭፍሮች ከተማ ሆይ፤

ጭፍሮችሽን አሰልፊ፤

ከበባ ተደርጎብናልና፤

የእስራኤልን ገዥ፣

ጒንጩን በበትር ይመቱታል።

2 “አንቺ ግን፣ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፤

ከይሁዳ ነገዶችመካከል ትንሿ ብትሆኚም፣

አመጣጡከጥንት፣

ከቀድሞ ዘመንየሆነ፣

የእስራኤል ገዥ፣

ከአንቺ ይወጣልኛል።”

3 ስለዚህ ወላዲቱ አምጣ እስክትገላገል ድረስ፣

እስራኤል ትተዋለች፤

የተቀሩት ወንድሞቹም፣

ተመልሰው ከእስራኤላውያን ጋር ይቀላቀላሉ።

4 በእግዚአብሔርኀይል

በአምላኩበእግዚአብሔርስም ታላቅነት፣

ጸንቶ ይቆማል፤ መንጋውንም ይጠብቃል።

በዚያን ጊዜ ኀያልነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ስለሚደርስ፣

ተደላድለው ይኖራሉ።

5 እርሱም ሰላማቸው ይሆናል።

ትድግናና ጥፋት

አሦራዊ ምድራችንን ሲወር፣

ምሽጐቻችንንም ጥሶ ሲገባ፣

ሰባት እረኞችን፣

እንዲያውም ስምንት አለቆችን እናስነሣበታለን።

6 የአሦርን ምድር በሰይፍ፣

የናምሩድን ምድርበተመዘዘ ሰይፍ ይገዛሉ፤

አሦራዊው ምድራችንን ሲወር፣

ዳር ድንበራችንን ሲደፍር፣

እርሱ ነጻ ያወጣናል።

7 የያዕቆብ ትሩፍ፣

በብዙ አሕዛብ መካከል

ከእግዚአብሔርዘንድ እንደሚወርድ ጠል፣

በሣር ላይ እንደሚጥል ካፊያ፣

ሰውን እንደማይጠብቅ፣

የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ሰው ይሆናል።

8 በዱር አራዊት መካከል እንዳለ አንበሳ፣

በእግሩ እየጨፈላለቀ እንደሚሄድ፣

የሰበረውን ማንም ሊነጥቀው እንደማይችል፣

በበግ መንጋ መካከል እንዳለ፣

እንደ ደቦል አንበሳ ሁሉ፣

የያዕቆብም ትሩፍ፣ በአሕዛብ ዘንድ፣ በብዙም ሕዝብ መካከል እንደዚሁ ይሆናል።

9 እጅህ በጠላቶችህ ላይ በድል አድራጊነት ከፍ ከፍ ትላለች፤

ጠላቶችህም ሁሉ ይጠፋሉ።

10 “በዚያን ጊዜ” ይላልእግዚአብሔር፤

“ፈረሶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤

ሠረገሎቻችሁን እደመስሳለሁ።

11 የምድራችሁን ከተሞች እደመስሳለሁ፤

ምሽጎቻችሁንም ሁሉ አፈርሳለሁ።

12 ጥንቈላችሁን አጠፋለሁ፤

ከእንግዲህም አታሟርቱም።

13 የተቀረጹ ምስሎቻችሁን፣

የማምለኪያ ዐምዶቻችሁንም ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤

ከእንግዲህ ለእጃችሁ ሥራ

አትሰግዱም።

14 የአሼራ ምስልን ዐምድከመካከላችሁ እነቅላለሁ፤

ከተሞቻችሁንም እደመስሳለሁ።

15 ያልታዘዙኝን አሕዛብ፣

በቍጣና በመዓት እበቀላቸዋለሁ።”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *