ምሳሌ 21

1 የንጉሥ ልብበእግዚአብሔርእጅ ነው፤

እርሱም እንደ ቦይ ውሃ ደስ ወዳሰኘው ይመራዋል።

2 ለሰው መንገዱ ሁሉ ቀና ይመስለዋል፤

እግዚአብሔርግን ልብን ይመዝናል።

3 ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ፍትሕን ማድረግ፣

በእግዚአብሔርዘንድ ተቀባይነት አለው።

4 ትዕቢተኛ ዐይን፣ እብሪተኛ ልብ፣

የክፉዎችም መብራት ኀጢአት ናቸው።

5 የትጒህ ሰው ዕቅድ ወደ ትርፍ ያመራል፤

ችኰላም ወደ ድኽነት ያደርሳል።

6 በሐሰተኛ አንደበት የተገኘ ሀብት፣

በኖ የሚጠፋ ተን፣ ለሞትም የሚያበቃ ወጥመድ ነው።

7 ክፉዎችን ዐመፃቸው ይጠራርጋቸዋል፤

ቅን ነገር ማድረግ አይወዱምና።

8 የበደለኛ መንገድ ጠማማ ነው፤

የንጹሕ ሰው ጠባይ ግን ቀና ነው።

9 ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር፣

በጣራ ላይ ጥግ ይዞ መኖር ይሻላል።

10 ክፉ ሰው ክፋትን አጥብቆ ይመኛል፤

ባልንጀራውም ከእርሱ ዘንድ ርኅራኄን አያገኝም።

11 ፌዘኛ ሲቀጣ፣ አላዋቂ ጥበብን ያተርፋል፤

ጠቢብ ሰው ቢማር ዕውቀትን ያገኛል።

12 ጻድቁየክፉዎችን ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል፤

ክፉዎችንም ያጠፋቸዋል።

13 ሰው የድኾችን ጩኸት ላለመስማት ጆሮውን ቢዘጋ፣

እርሱም ይጮኻል፤ መልስም አያገኝም።

14 በስውር የተደረገ ስጦታ ቊጣን ያበርዳል፤

በጒያ የተሸሸገ እጅ መንሻም ታላቅ ቊጣን ጸጥ ያደርጋል።

15 ፍትሕ ሲሰፍን ጻድቁን ደስ ያሰኘዋል፤

ክፉ አድራጊዎችን ግን ያሸብራል።

16 የማስተዋልን መንገድ የሚስት ሰው፣

በሙታን ጉባኤ ያርፋል።

17 ቅንጦትን የሚወድ ይደኸያል፤

የወይን ጠጅና ዘይት የሚወድም ባለጠጋ አይሆንም።

18 ክፉ ሰው ለጻድቅ፣

ወስላታም ለቅን ሰው ወጆ ይሆናል።

19 ከጨቅጫቃና ከቊጡ ሚስት ጋር ከመኖር፣

በምድረ በዳ መኖር ይሻላል።

20 በጠቢብ ቤት ምርጥ ምግብና ዘይት ተከማችቶ ይገኛል፤

ተላላ ሰው ግን ያለ የሌለውን ያሟጥጣል።

21 ጽድቅንና ፍቅርን የሚከተል፤

ሕይወትን ብልጽግናንናክብርን ያገኛል።

22 ጠቢብ የኀያላንን ከተማ ቅጥር ጥሶ ይገባል፤

መታመኛ ምሽጋቸውንም ያፈርሳል።

23 አንደበቱንና ምላሱን የሚቈጣጠር፣

ራሱን ከመቅሠፍት ይጠብቃል።

24 ትዕቢተኛና ኵሩ ሰው፣ ኋፌዘኛቃ ይባላል፤

በጠባዩም እብሪተኛ ነው።

25 ታካችን የሚገድለው ምኞቱ ነው፤

እጆቹ መሥራት አይፈልጉምና።

26 ክፉ ሰው ቀኑን ሙሉ ይመኛል፤

ጻድቅ ግን አንዳች ሳያስቀር ይሰጣል።

27 የክፉ ሰው መሥዋዕት አጸያፊ ነው፤

በክፉ ዐላማ ሲያቀርብማ የቱን ያህል አስከፊ ይሆን!

28 ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፤

እውነቱን የሚናገር ግን ጸንቶ ይኖራል።

29 ክፉ ሰው በዐጒል ድፍረት ይቀርባል፤

ቅን ሰው ግን አደራረጉን ያስተውላል።

30 እግዚአብሔርንለመቋቋም የሚያስችል፣

አንዳችም ጥበብ ማስተዋልና ዕቅድ የለም።

31 ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤

ድል ግንከእግዚአብሔርዘንድ ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *