1 በቴቁሔ ከነበሩት እረኞች መካከል አንዱ የሆነው አሞጽ፣ ዖዝያን የይሁዳ ንጉሥ በነበረ ጊዜ እንዲሁም የዮአስልጅ ኢዮርብዓም የእስራኤል ንጉሥ በነበረ ጊዜ፣ ይኸውም የምድር መናወጥ ከመሆኑ ከሁለት ዓመት በፊት ስለ እስራኤል ያየውና የተናገረው ቃል ይህ ነው፤
2 እርሱም እንዲህ አለ፤
“እግዚአብሔርከጽዮን ድምፁን ከፍ አድርጎ ያሰማል፤
ከኢየሩሳሌምም ያንጐደጒዳል፤
የእረኞች ማሰማሪያዎች ደርቀዋል፤
የቀርሜሎስም ዐናት ጠውልጎአል።”
በእስራኤል ጐረቤቶች ላይ የተሰጠ ፍርድ
3 እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤
“ስለ ሦስቱ የደማስቆ ኀጢአት፣
ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤
የብረት ጥርስ ባለው ማሄጃ፣ ገለዓድን
አሂዳለችና፤
4 የወልደ አዴርን ምሽጎች እንዲበላ፣ በአዛሄል
ቤት ላይ እሳት እሰዳለሁ።
5 የደማስቆን በሮች እሰባብራለሁ፤
በቤት ዔደን በትር የያዘውን፣
በአዌንሸለቆ ያለውንንጉሥ እደመስሳለሁ፤
የሶርያም ሕዝብ ተማርኮ ወደ ቂር ይሄዳል”
ይላልእግዚአብሔር።
6 እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤
“ስለ ሦስቱ የጋዛ ኀጢአት፣
ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤
ሕዝቡን ሁሉ ማርካ በመውሰድ፣
ለኤዶም ሸጣለችና።
7 ምሽጎቿን እንዲበላ፣
በጋዛ ቅጥሮች ላይ እሳት እሰዳለሁ።
8 በአስቀሎና በትር የያዘውን፣
የአሸዶድንም ንጉሥእደመስሳለሁ፤ በፍልስጥኤም ካሉት የመጨረሻው ሰው
እስኪሞት ድረስ፣
እጄን በአቃሮን ላይ እዘረጋለሁ፤”
ይላል ጌታእግዚአብሔር።
9 እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤
“ስለ ሦስቱ የጢሮስ ኀጢአት፣
ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም።
የወንድማማችነትን ቃል ኪዳን በማፍረስ፣
ሕዝቡን ሁሉ ማርካ ለኤዶም ሸጣለችና።
10 ምሽጎችዋን እንዲበላ፣
በጢሮስ ቅጥሮች ላይ እሳት እሰዳለሁ።”
11 እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤
“ስለ ሦስቱ የኤዶም ኀጢአት፣
ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤
ርኅራኄንበመንፈግ፣
ወንድሙን በሰይፍ አሳዶታልና፤
የቊጣውንም ነበልባል ሳይገድብ፣
መዓቱን ሳያቋርጥ አውርዶበታልና፤
12 የባሶራን ምሽጎች እንዲበላ፣
በቴማን ቅጥሮች ላይ እሳት እሰዳለሁ።”
13 እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤
“ስለ ሦስቱ የአሞን ኀጢአት፣
ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤
ድንበሩን ለማስፋት፣
የገለዓድን ነፍሰ ጡር ሴቶች ሆድ ቀዶአልና።
14 በጦርነት ቀን በጩኸት ውስጥ፣
በማዕበል ቀን በዐውሎ ነፋስ ውስጥ፣
ምሽጎቿን እንዲበላ፣
በረባት ቅጥሮች ላይ እሳት እሰዳለሁ።
15 ንጉሥዋከሹማምንቱ ጋር፣
በአንድነት ተማርኮ ይሄዳል፣”
ይላልእግዚአብሔር።