አሞጽ 4

እስራኤል ወደ እግዚአብሔር አልተመለሰም

1 እናንተ በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ የባሳን ላሞች፣

ድኾችን የምትጨቁኑና ችግረኞችን የምታስጨንቁ፣

ባሎቻችሁንም፣ “መጠጥ አቅርቡልን”

የምትሉ ሴቶች ይህን ቃል ስሙ፣

2 ጌታእግዚአብሔርበቅድስናው እንዲህ ሲል ምሎአል፤

“እነሆ፤ በመንጠቆ ተይዛችሁ የምትወሰዱበት

ትሩፋናችሁ እንኳ በዓሣ መንጠቆ

የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል።

3 እያንዳንዳችሁ በቅጥሩ በተነደለው መሽሎኪያ

ወደ ሬማንምትጣላላችሁ፤”

ይላልእግዚአብሔር።

4 “ወደ ቤቴል ሂዱና ኀጢአትን ሥሩ፤

ወደ ጌልገላም ሂዱና ኀጢአትን አብዙ፤

በየማለዳው መሥዋዕቶቻችሁን፣

በየሦስቱዓመት ዐሥራታችሁን አቅርቡ።

5 እርሾ ያለበትን እንጀራ የምሥጋና

መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ፤

በፈቃዳችሁም በምታቀርቡት ቊርባን ተመኩ፤

እናንት እስራኤላውያን በእነርሱም ተኵራሩ፤ ማድረግ የምትወዱት ይህን ነውና፤”

ይላል ጌታእግዚአብሔር።

6 በየከተማው ሆዳችሁንባዶ አደረግሁት፤

በየመንደሩም የምትበሉትን

አሳጣኋችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም”

ይላልእግዚአብሔር።

7 “መከር ሊደርስ ሦስት ወር ሲቀረውም፣

ዝናብ ከለከልኋችሁ፤

በአንዱ ከተማ ላይ አዘነብሁ፤

በሌላው ላይ ግን እንዳይዘንብ

አደረግሁ፤ አንዱ ዕርሻ ሲዘንብለት፣

ሌላው ዝናብ አጥቶ ደረቀ።

8 ሰዎች ውሃ ፍለጋ ከከተማ ወደ ከተማ ባዘኑ፣

ይሁን እንጂ ጠጥተው አልረኩም፤

እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤”

ይላልእግዚአብሔር።

9 “የአትክልትና የወይን ቦታዎቻችሁን ብዙ ጊዜ መታሁ፤

በዋግና በአረማሞም አጠፋኋቸው፤

አንበጦችም የበለስና የወይራ ዛፎቻችሁን በሉ፤

እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤”

ይላልእግዚአብሔር።

10 “በግብፅ ላይ እንዳደረግሁት፣

መቅሠፍትን ላክሁባችሁ፤

ከተማረኩት ፈረሶቻችሁ ጋር፣

ጐልማሶቻችሁን በሰይፍ ገደልሁ፤

የሰፈራችሁ ግማት አፍንጫችሁ እንዲገባ አደረግሁ፤

እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም”

ይላልእግዚአብሔር።

11 “ሰዶምንና ገሞራን እንደ ገለበጥኋቸው፣

አንዳንዶቻችሁን ገለበጥሁ፤

ከእሳት እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤

እናንተ ግን ወደ እኔአልተመለሳችሁም፤”

ይላልእግዚአብሔር።

12 “ስለዚህ እስራኤል ሆይ፤ እንደዚህ አደርግብሃለሁ፤

እንደዚህም ስለማደርግብህ፣ እስራኤል ሆይ፤

አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ።”

13 ተራሮችን የሚሠራ፣

ነፋስን የሚፈጥር፣

ሐሳቡንም ለሰው የሚገልጥ፣

ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፣

የምድርንም ከፍታዎች የሚረግጥ፣

ስሙ የሰራዊት አምላክእግዚአብሔርነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *