የውዳሴ መዝሙር
1 በዚያን ቀን እንዲህ ትላለህ፤
“እግዚአብሔርሆይ፤
ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤
አሁን ግን ከቍጣህ ተመለስህ፤
ደግሞም አጽናንተኸኛልና እወድስሃለሁ።
2 እነሆ፣ እግዚአብሔር ድነቴ ነው፤
እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤
ጌታእግዚአብሔርብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤
ድነቴም ሆኖአል።”
3 ከድነቴ ምንጮች
ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ።
4 በዚያን ቀን እንዲህ ትላላችሁ፤
“እግዚአብሔርንአመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤
ያደረገውንም በአሕዛብ መካከል አስታውቁ፤
ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱንም ዐውጁ።
5 ለእግዚአብሔርዘምሩ፤ ታላቅ ሥራ ሠርቶአልና፤
ይህም ለዓለም ሁሉ ይታወቅ።
6 የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ እልል በሉ፤
በደስታም ዘምሩ፤
በመካከላችሁ ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ነውና።