ኢሳይያስ 20

በግብፅና በኢትዮጵያ ላይ የተነገረ ትንቢት

1 ዋናው የጦር አዛዥበአሦር ንጉሥ በሳርጎን ተልኮ፣ የአዛጦንን ከተማ ወሮ በያዘበት ዓመት፣

2 በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን፣ “ማቁን ከሰውነትህ፣ ጫማህን ከእግርህ አውልቅ” ሲል ተናገረው። እርሱም እንዲሁ አደረገ፤ ዕርቃኑንና ባዶ እግሩን ተመላለሰ።

3 ከዚያምእግዚአብሔርእንዲህ አለ፤ “ባሪያዬ ኢሳይያስ ሦስት ዓመት በግብፅና በኢትዮጵያ ለምልክትና ለማስጠንቀቂያ ዕርቃኑንና ባዶ እግሩን እንደሄደ፣

4 እንዲሁ የአሦር ንጉሥ ወጣትና ሽማግሌ የሆኑትን የተማረኩ ግብፃውያንንና የተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን ዕርቃናቸውንና ባዶ እግራቸውን ይወስዳቸዋል፤ መቀመጫቸውን ገልቦ በመስደድም ግብፅን ያዋርዳል።

5 በኢትዮጵያ ተስፋ ያደረጉ፣ በግብፅ የተመኩ ይፈራሉ፤ ይዋረዳሉም።

6 በዚያ ቀን በዚህ ባሕር ዳርቻ የሚኖረው ሕዝብ፣ ‘የተመካንባቸው፣ ከአሦር ንጉሥ ለማምለጥና ነጻ ለመውጣት የተሸሸግንባቸው ምን እንደ ደረሰባቸው ተመልከቱ እንግዲህ እኛስ እንዴት እናመልጣለን?’ ይላል።”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *