1 በዚያን ቀን ሰባት ሴቶች
አንዱን ወንድ ይዘው፣
“የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤
የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤
በአንተ ስም ብቻ እንጠራና፣
ውርደታችንን አስቀርልን” ይሉታል።
የእግዚአብሔር ዛፍ ቅርንጫፍ
2 በዚያን ቀንየእግዚአብሔርዛፍ ቅርንጫፍ ያማረና የከበረ ይሆናል፤ የምድሪቱም ፍሬ ከጥፋት ለተረፈው የእስራኤል ወገን ኵራትና ክብር ይሆናል።
3 በጽዮን የቀሩት፣ በኢየሩሳሌምም የተረፉት፣ በኢየሩሳሌም በሕይወት ከተመዘገቡት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ።
4 ጌታ የጽዮንን ሴቶች እድፍ ያጥባል፤ ኢየሩሳሌምንም ከተነከረችበት ደም በፍርድና በሚያቃጥል መንፈስያነጻታል።
5 ከዚያምእግዚአብሔርበጽዮን ተራራ ላይና በዚያ በሚሰበሰቡትም ሁሉ ላይ በቀን ደመናንና ጢስን፣ በሌሊትም የሚንበለበለውን የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤ በክብሩ ሁሉ ላይ መጋረጃ ይሆናል፤
6 ከቀኑ ሙቀት ጥላና መከለያ፣ ከውሽንፍርና ከዝናብም መጠጊያና መሸሸጊያ ስፍራ ይሆናል።