ኢሳይያስ 42

የእግዚአብሔር አገልጋይ

1 “ደግፌ የያዝሁት አገልጋዬ፣

በእርሱም ደስ የሚለኝ ምርጤ ይህ ነው፤

መንፈሴን በእርሱ ላይ አደርጋለሁ፤

ለአሕዛብም ፍትሕን ያመጣል።

2 አይጮኽም፣ ቃሉን ከፍ አያደርግም፤

ድምፁን በመንገድ ላይ በኀይል አያሰማም።

3 የተቀጠቀጠ ሸምበቆ አይሰብርም፤

የሚጤስም የጧፍ ክር አያጠፋም፤

ፍትሕን በታማኝነት ያመጣል።

4 ፍትሕን በምድር እስኪያመጣ ድረስ፣

አይደክምም፤ ተስፋም አይቈርጥም፤

ደሴቶች በሕጉ ይታመናሉ።”

5 ሰማያትን የፈጠረ፣ የዘረጋቸውም፣

ምድርንና በውስጧ ያሉትን ሁሉ ያበጀ፣

ለሕዝቧ እስትንፋስን፣

ለሚኖሩባትም ሕይወትን የሚሰጥ፣

ጌታእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤

6 “እኔእግዚአብሔርበጽድቅ ጠርቼሃለሁ፤

እጅህንም እይዛለሁ፤

እጠብቅሃለሁ፤

ለሕዝቡ ቃል ኪዳን፣

ለአሕዛብም ብርሃን አደርግሃለሁ።

7 የዕውሮችን ዐይን ትከፍታለህ፤

ምርኮኞችን ከእስር ቤት፣

በጨለማ የተቀመጡትንም ከወህኒ ታወጣለህ።

8 “እኔእግዚአብሔርነኝ፤ ስሜም ይህ ነው፤

ክብሬን ለሌላ፣

ምስጋናዬንም ለጣዖት አልሰጥም።

9 እነሆ፤ የቀድሞው ነገር ተፈጽሞአል፤

እኔም አዲስ ነገር እናገራለሁ፤

ከመብቀሉም በፊት፣

ለእናንተ አስታውቃለሁ።

ለእግዚአብሔር የውዳሴ መዝሙር

10 እናንት ወደ ባሕር የምትወርዱ፣ በዚያም ያላችሁ ሁሉ፣

ደሴቶችና በዚያ የምትኖሩ በሙሉ፣

ለእግዚአብሔርአዲስ መዝሙር፣

ከምድር ዳርቻም ምስጋናውን ዘምሩ።

11 ምድረ በዳውና ከተሞቹ ድምፃቸውን ከፍ ያድርጉ፤

ቄዳር ያለችበት መንደር ደስ ይበለው፤

የሴላ ሕዝቦች በደስታ ይዘምሩ፤

ከተራሮችም ራስ ላይ ይጩኹ።

12 ክብርለእግዚአብሔርይስጡ፤

ምስጋናውንም በደሴቶች ያውጁ።

13 እግዚአብሔርእንደ ኀያል ሰው ይዘምታል፤

እንደ ተዋጊ በወኔ ይነሣል፤

የቀረርቶ ጩኸት ያሰማል፤

ጠላቶቹንም ድል ያደርጋል።

14 “ለረጅም ጊዜ ዝም አልሁ፤

ጸጥ አልሁ፤ ራሴንም ገታሁ፤

አሁን ግን ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣

እጮኻለሁ፤ ቁና ቁና እቃትታለሁ፤ እተነፍሳለሁ።

15 ተራራውንና ኰረብታውን አፈርሳለሁ፤

ዕፀዋቱን ሁሉ አደርቃለሁ፤

ወንዙንም ደሴት አደርጋለሁ፤

ኵሬውን አደርቃለሁ።

16 ዕውሮችን በማያወቁት መንገድ

እመራቸዋለሁ፤

ባልተለመደ ጐዳና እወስዳቸዋለሁ።

ጨለማውን በፊታቸው ብርሃን አደርጋለሁ፤

ጐርባጣውን ስፍራ አስተካክላለሁ።

ይህን አደርጋለሁ፤

አልተዋቸውም።

17 በጣዖት የሚታመኑ ግን፣

ምስሎችን፣ ‘አምላኮቻችን ናችሁ’ የሚሉ፣

ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ ፈጽመው ይዋረዳሉም።

ዕውሯና ደንቈሮዋ እስራኤል

18 “እናንት ደንቈሮዎች ስሙ፤

እናንት ዕውሮች እዩ፤ ተመልከቱም።

19 አገልጋዬ እንጂ፣ ሌላ ዕውር ማን አለ?

ከምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ማን ደንቈሮ አለ?

ለእኔ ታማኝ እንደሆነ ሰው የታወረ፣

እንደእግዚአብሔርስአገልጋይ ዕውር ማነው?

20 ብዙ ነገርን አያችሁ፤ ነገር ግን አላስተዋላችሁም፤

ጆሮአችሁ ክፍት ነው፤ ነገር ግን ምንም አትሰሙም።”

21 እግዚአብሔርስለ ጽድቁ ሲል፣

ሕጉን ታላቅና የተከበረ በማድረግ ደስ

አለው።

22 ይህ ሕዝብ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ፣

በጒድጓድ ውስጥ የተጠመደበት፣

በወህኒ ቤት የተዘጋበት ነው፤

ተበዝብዘዋል፣

የሚያድናቸውም የለም፤

ተማርከዋል፣

“መልሷቸው” የሚልም የለም።

23 ከእናንተ ይህን የሚሰማ፣

ለሚመጣውም ጊዜ አስተውሎ የሚያደምጥ ማነው?

24 ያዕቆብን ለዝርፊያ፣

እስራኤልን ለምርኮ የዳረገ ማነው?

በኀጢአት የበደልነው፣

እግዚአብሔርአይደለምን?

መንገዱን ለመከተል፣

ለሕጉም መታዘዝ አልፈለጉምና።

25 ስለዚህ የሚነድ ቍጣውን፣

የጦርነትንም መዓት አፈሰሰባቸው፤

በእሳት ነበልባል ከበባቸው፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም፤

አቃጠላቸው፤ እነርሱ ግን ልብ አላሉም።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *